የፓስፖርት አገልግሎት
ሊሴ ፓሴ አገልግሎት
የቪዛ አገልግሎት
ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ አገልግሎት
የውክልና የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት
ቅልለው ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ ቀረጥና ታክስ ከፍለው እቃዎች ለማስገባት
If you are not able to read this page, please download Amharic Font click here. 
 

እባክዎ የኮንሱላር አገልግሎቶች በሙሉ በፖስታ ቤት ብቻ የምናስተናግድ መሆኑን ይገንዘቡ !!!  ሆኖም ግን በዲሲ እና  አካቢዋ የምትኖሩ በአካል በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡ እባክዎ ኮንሱላር ሰርቪስን የተመለከቱ ቅሬታዎችን እና አስተያየትዎን በኢሜይል አድራሻችን consular@ethiopianembassy.org ይላኩልን !!!

ፓስፖርት ለማመልከት

እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ይላኩ፡፡ አዲሱ ማሽን ሪደብል ፓስፖርት በኢምባሲያችን በኩል አገር ቤት ተልኮ ስለሚዘጋጅ እባክዎ ከጉዞ ቀን ወይም ከታደሰ ፓስፖርት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ከመጠየቅዎ ቢያንስ 45 ቀናት አስቀድመው ማመልከት ይጠበቅቦታል፡፡

 • አዲሱ ማሽን ሪደብል ፓስፖርት ለማግኘት የጣት አሻራ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደም አዲሱን ፓስፖርት ሲወስዱ የጣት አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግዎትም፡፡ እድሜአቸው ከ14 አመት በታች የሆኑ ህጻናት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም፤ ሆኖም ከዚህ ቀደም ከ14 ዓመት በታች በመሆናቸው ምክንያት ያለ አሻራ አዲሱ ፓስፖርት ተዘጋጅቶላቸው ከነበረና አሁን ከ14ዓመትና በላይ ከሆኑ የጣት አሻራ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

 • ፓስፖርትዎ ተዘጋጅቶ እስከሚደርስዎ ድረስ መቆየት የማይችሉና በተለያየ አጣዳፊ ምክንያቶች በአስቸኳይ ወደ አገርቤት መሄድ ከፈለጉ ወደ አገር ቤት መግቢያ ብቻ የሚያገለግለውን ሊሴ ፓሴ ብቻ (የሊሴ ፓሴ አገልግሎት የሚለውን ይክፈቱ) ወስደው ከአገር ቤት ፓስፖርት ማመልከት ይገባዎታል።

 • የፓስፖርትና የሊሴ ፓሴ ማመልከቻ በአንድ ላይ ማቅረብ ወይም የፓስፖርትዎ ማመልከቻ ከኤምባሲው ወደ አገር ቤት ከተላከ ከአንድ ወርና ከዚያ በላይ ሳይሆን ሊሴ ፓሴ ማመልከት አይቻልም። ነገር ግን ኢምባሲው ማመልከቻዎን አገር ቤት ከላከ አንድ ወርና ከዚያ በላይ ከሆነና ፓስፖርቱን ሳይረከቡ ጉዞዎ ከደረሰ ሊሴ ፓሴ ወስደው አገር ቤት ሲደርሱ ከኢሚግሬሽን ፓስፖርትዎን መረከብ ይችላሉ።

 • ኢምባሲው ፓስፖርትዎን ለማዘጋጀት ተጨማሪ ማስረጃዎች እንዲያቀርቡ ሲጠይቅ እባክዎ በተነገረዎት በሳምንት ግዜ ውስጥ ማስረጃውን ይላኩልን፡፡ ሆኖም ማስረጃውን እንዲልኩ ለ3ኛ ጊዜ ተገልጾልዎት ከሆነና በወቅቱ ካላቀረቡ ፋይልዎ ተመላሽ ተደርጎ እንደ አዲስ ማመልከት ይጠበቅቧታል፡፡

 • ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL መሆን ይገባዋል፡፡ የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱም ሆነ የተዘጋጀለዎት ሰነድ ወደ እርሶ ተመላሽ ለመደረጉ ባለዎት የፖስታ Tracking Number በመጠቀም ማጣራት ሰለሚችሉ ይህንኑ መረጃ ለማረጋገጥ ወደ ኢምባሲው መደወል አይጠበቅብዎትም፡፡  የተዘጋጀለዎትን ፓስፖርት ከኢሚግሬሽን በተረከብንበት እለት በላኩልን የመመለሻ ፖስታ ወደ እርሶ ይላካል፡፡

አገልግሎቱ ያለቀ ፓስፖርት ለመቀየር/ለማሳደስ

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1)

4 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)

2)

ለመቀየር ወይም ለማሳደስ የተፈለገው ዋናው ፓስፖርት ማቅረብ

3)

ለመቀየር ወይም ለማሳደስ የተፈለገው ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ ማቅረብ

4)

በአሜሪካን አገር የሚኖሩበትን ስታተስ የሚያሳይ የግሪን ካርድ  ወይም ግሪን ካርድ ከሌለዎት የ I-94 ወይም የስራ ፍቃድ ማስረጃ በሁለት ኮፒ

5)

የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ መኒ ኦርደር /Money Order/ ሆኖ

ተራ ቁ.

ፓስፖርት

የአገልግሎት ክፍያ በዶላር

1

32 ገፅ ያለው ፓስፖርት

60 ዶላር

2

64 ገፅ ያለው ፓስፖርት

110 ዶላር

6)

የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅፅ (Form) ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ፤ ሆኖም ድርጅቱ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅፅ ከሌለው በኢምባሲያችን በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ ቅፅ (click here to download Fingerprint Capture FORM) መጠቀም ይቻላል፡፡

7)

መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት (click here to download FORM)

8)

አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ

በጠፋ ፓስፖርት ምትክ አዲስ ፓስፖርት ለመቀየር

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1)

4 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)

2)
የቀድሞ ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ ማቅረብ

3)

በአሜሪካን አገር የሚኖሩበትን ስታተስ የሚያሳይ የግሪን ካርድ  ወይም ግሪን ካርድ ከሌለዎት የ -94 ኮፒ ወይም የስራ ፍቃድ ማስረጃ በሁለት ኮፒ

4)

የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ መኒ ኦርደር /Money Order/ ሆኖ

 
 • ለመጀመሪያ ጊዜ ምትክ ፓስፖርት ሲሰጥ ለባለ 32 ገፅ $90፣ ለባለ 64 ገፅ $165፤
 • ለሁለተኛ ጊዜ ምትክ ፓስፖርት ሲሰጥ ለባለ 32 ገፅ $120፣ ለባለ 64 ገፅ $220፤
 • ለሶስተኛ ጊዜ ምትክ ፓስፖርት በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ ጥያቄ ከቀረበ ለባለ 32 ገፅ $180፣ ለባለ 64 ገፅ $330፤

5)

የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅፅ (Form) ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ፤ ሆኖም ድርጅቱ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅፅ ከሌለው በኢምባሲያችን በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ ቅፅ (click here to download Fingerprint Capture FORM) መጠቀም ይቻላል፡፡

6)

መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት(click here to download FORM)

7) አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
   
በውጭ አገር የሚኖሩ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያኖችን ህጋዊ ሰነድ እንዲኖራቸው የሚያደርግ አገልግሎት
1 ምንም አይነት ሰነድ ሳይኖራቸው በተለያዩ አገራት ለሚኖሩ የኢት/ያ ፓስፖርት እና ሊሴ ፓሴ ጠያቂዎች አገልግሎት አሰጣጥ ለመወሰን የወጣ አሰራር በተመለከተ፤
2 በሚኖሩበት አገር በኢትዮጵዊነት የጥገኝነት ጥያቄ አቅርቦ ተቀባይነት ያገኙ/ያላገኙ ሰነድ አልባ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ጠያቂዎች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባቸዋል።
 
 • አመልካቹ/ቿ ኢትዮጵያዊ መሆኔ ተጣርቶ ፓስፖርት እንዲሰጠኝ የሚል ማመልከቻ በራሱ ፍላጎት ፈርሞ ሲያቀርብ እና ያመለከተበት የአገራችን ኢምባሲ ተቀማጭ የሆነበት ወይም የሚሸፍነው ወይም የተወከለበት አገር ነዋሪ መሆኑን የሚይሳይ ማስረጃ ማቅረብ።

ምንም አይነት የኢትዮጵያ ፓስፖርት ላላወጡ
 
 • ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን የፓሰፖርት መጠየቂያ ቅጽ ጋር እንዲያየዙ የተጠየቁ ሰነደችን አያይዞ ማቅረብ።
 
 • በተዘጋጀው የአሻራ መወሰጃ ቅጽ በአግባቡ የጣት አሸራ በመዉሰድና ሁለት የፓሰፖርት መጠን ያለዉ ጉርድ ፎቶ ግራፍ በማያያዝ ማቅረብ።
 
 • አመልካቹ በሚኖርበትን አገር የመኖርያ ፍቃድ ወይም ሌላ የጉዞ ሰነድ ካለዉ የመኖርያ ፍቃዱን ወይም የጉዞ ሰነዱንና ኮፒዉን አያይዞ ማቅረብ።
3 ቀደም ሲል የኢትዮጵያን ፓስፖርት ወስደዉ የነበሩ ወይም የጠፋባቸዉ።
 
 • ለዚህ ዓላማ በተዛጋጀዉ ቅጽ መሰረት የማመልካቻ ቅጽን መልቶ የተጠየቁ ሰነዶችን ማያያዝና ማቅረብ።
 
 • የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወስደዉ የነበሩ ፓስፖርቱ ያላቸዉና ጥገኝነት ለማገኘት ሲሉ የደበቁ ፓስፖርቱንና ኮፒዉን ማያያዝና ማቅረብ።
 
 • ፓስፖርቱን ወስደዉ የነበሩ ነገረ ግን ኣሁን በእጃቸዉ የሌለ ኮሆነ የቀድሞዉን ፓስፖርት ቁጥርና የተሰጠበትን ዓመተ ምህረት በመጥቀስ ማያያዝ።
 
 • የጣት ኣሸራ በኣግባቡ በኣሸራ መዉሰጃ ቅጹ ተመልቶና ሁለት የፓስፖርት መጠን ያለዉ ጉርድ ፎቶ ግራፍ በማያያዝ ማቅረብ።

4

የጣት ኣሸራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ አመልካቶች በአቅራቢያችሁ በሚገኝ ፖሊስ ጣብያ ወይም የጣት አሽራ ለመዉሰድ ፍቃድ ካላቸዉ ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሸራ መዉሰጃ ቅጽ (form) ላይ አሸራዎን ሰጥቶተዉ ዋናዉንና ኮፒዉን መላክ። ሆኖም ድርጅቱ የጣት አሸራ መዉሰጃ ቅጽ ከሌለዉ በኢምባሲዉ በኩል የተዛጋጀዉን የጣት አሻራ መዉሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ።(click here to download finger print capture form)

5 ሰሰት (3) የፓስፖርት መጠን ያለዉና ቢያንስ ከ 6ወር ወዲህ የተነሱት ፈቶ ግራፍ ሁለቱ ጀሮዎች የሚታዩ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባዉ ስም የተፃፈበት።

6

የአልግሎት ክፍያ ምንም ዓይነት ፓስፖርት ያላወጡ አዲስ ጠያቂዎች ከሆኑ $60 ደለር የጠፋባቸዉ ከሆኑ ግን $90 ደላር ለኢምባሲ የተፃፈ መኒ ኦርደር (Money order) መላክ።

7 አድራሻዎ የተፃፈበት መመለሻ ፖስታ (Tracking Number ) ያለዉ USP OR USPS EXPRESS MAIL ) ከነ ቴምብሩ አብሮ መላክ።

8

ለዚ የተዛጋጀዉ ፎርም (form or Application Click and Download) ያድርጉ በጥንቃቄ ይሙሉት።

እንዲሁም በኢምግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ የጉዞ ሰነድ የአመልካቹ ቅድመ ታሪክ የሚሞላበት ቅፅ ለማግኘት (Click Here to Download the form)

በጥንቃቄ ይሙሉት።


እባክዎ ኮንሱላር ሰርቪስን የተመለከቱ ቅሬታዎችን እና አስተያየትዎን በኢሜይል አድራሻችን consular@ethiopianembassy.org ይላኩልን !!!

INVESTING IN ETHIOPIA

»
Overviews
»
10 Reason Invest in Ethiopia
»
Agriculture
»
Floricultures
»
Textiles
»
Leather and Leather products
»
Mining
»
Briefing for Tour Operators

VISTING IN ETHIOPIA

»
Overviews
»
Filming in Ethiopia
»
Ethiopia Tourism
»
Tour Operators

FOR THE MEDIA

»
Ethiopia and the U.S.
»
Ambassador's Speeches
»
Ministry of Foreign Affairs
»
Ethiopia in the Media

NGO Matters Section

»
Contact Person
»
Adoption an Ethiopian Child
»
Registering an NGO (PDF)
Community | About Ethiopia | Investing in Ethiopia | Visting Ethiopia | For Media
Other Resources | Site Index | Contact Us

Embassy of Ethiopia © 2008, 3506 International Dr., NW Washington, D.C. 20008 (202) 364-1200/ (202) 364-1200 more