በWalters Art Museum የተዘጋጀው የኢትዮጵያን ጥበባዊ ትውፊቶች የሚያሳይ ኤግዚብሽን እየታየ ነው።


በአሜሪካ በሜሪላንድ ግዛት፣ በባልቲሞር ከተማ የሚገኘው Walters Art Museum ከጥንት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን የኢትዮጵያን ጥበባዊ ትውፊቶች የሚያሳይ ኤግዚቢሽን አዘጋጅቶ ለእይታ አቅርቧል። በኤግዚብሽኑ ላይ ከ200 በላይ ቅርሶችና ጥበባዊ ስራዎች ለእይታ ቀርበዋል። ኤግዚብሽኑ ዘመናትን ያስቆጠረ የኢትጵያን ባህላዊ፣ ሐይማኖታዊ እና ታሪካዊ ስራዎችን ለማሳየት ያለመ ሲሆን፣ አዘጋጆቹ ኤግዚብሽኑን ለማዘጋጀት ሰባት ዓመታት የወሰደ መሆኑን ገልጸዋል።
አዘጋጆቹ አገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በባህልና በሐይማኖት ዙሪያ ያላትን ታሪካዊ ትውፊት በመፈተሽ፣ የኢትዮጵያውያን አርቲስቶች እና ማህበረሰቦች የቅርብ እና የሩቅ ባህሎች ጋር የሚገናኙበት እና ሀሳብ የሚለዋወጡባቸው መንገዶች ለማመላከት የተዘጋጀ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። በተጨማሪም ኤግዚብሽኑ ስኬት በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢ.ፊ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ የኢትዮጵያን የኪነ-ጥበብ ስራዎች ከኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ተሳብስበው እንዲቀርቡ በማገዝ ላደረገው ትብብር ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

ክቡር የሚሰዮኑ መሪ በኩላቸው የኢትየጵያን ባህል፣ ታሪክ እና ሐይማኖታዊ ትውፊቶችን የሚያሳይ የኪነ-ጥበብ ስራዎች ያካተተ ኤግዚብሽን ለህዝብ ለዕይታ እንዲቀርብ ላደረጉ አካላት ላቀ ያለ ምስጋና አቅርበው፣ አገራችን ኢትዮጵያ በኪነ-ጥበብ ስራዎችና በባህል ልውውጦች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከተች አስረድተዋል። በተጨማሪም ኤግዚብሽኑ የሀገራችንን ገፅታ ለመገንባት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ያነሱ ሲሆን፣ ኤግዚብሽኑ ስለ ኢትዮጵያ ብዙ የማያውቁ አሜሪካዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አገሪቱን በመጎብኘት ይበልጥ ለማወቅ ፍላጎት እንዲያድርባቸው የሚያነሳሳ መሆኑን ገልጸዋል። ክቡር የሚሲዮኑ መሪ ኢትዮጵያ በበርካታ የቱሪዝም መስህቦች የታደለች አገር መሆኗንና አስታውሰው በተለይ የውጭ አገራት ዜጎች ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በመጨረሻም ክቡር አምባሳደሩ የሁለቱ አገራት ህዝቦች የባህልና ታሪክ ልውውጥ እና ትስስር ለማሳደግ ኤምባሲው በቀጣይነት ከሙዚየሙ ጋር በጋራ ለመስራት ፍቃደኛ መሆኑን አስረድተዋል።
ለዕይታ የቀረበውን ኤግዚቢሽን የሚሲዮኑ መሪ ክቡር አምባሳደር ስለሺ በቀለ እና የሚሲዮኑ ዲፕሎማቶች የካቲት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ጎብኝተዋል። ይህም ኤግዚቢሺን እ.ኤ.አ. አስከ ማርች 3 ቀን 2024 ድረስ ለዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *