ቅልለው ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ ቀረጥና ታክስ ከፍለው እቃዎች ለማስገባት ለሚፈልጉ አመልካቾች

  • እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንሰጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ይላኩ፡፡

  • አገልግሎቱን ለመጠየቅ አምስት አመትና ከዚያ በላይ በውጭ አገር የኖሩ መሆን ይኖርብዎታል፡፡

  • በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ አገልግሎቱን መጠየቅ አይችሉም፡፡

  • ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL መሆን ይገባዋል፡፡ የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱም ሆነ የተዘጋጀለዎት ሰነድ ወደ እርሶ ተመላሽ ለመደረጉ ባለዎት የፖስታ Tracking Number በመጠቀም ማጣራት ሰለሚችሉ ይህንኑ መረጃ ለማረጋገጥ ወደ ኢምባሲው መደወል አይጠበቅብዎትም፡፡

አገልግሎቱ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟሉ

1)

አምስት አመትና ከዚያ ላይ በውጭ አገር መቆየትዎን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ፣ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ እና ሌላ ማስረጃ ማቅረብ

2)

ኢትዮጵያዊ ከሆኑ አገልግሎቱ ያላበቃ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ ከሆኑ አገልግሎቱ ያላበቃ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ በሁለት ኮፒ

3)

ግሪን ካርድ በሁለት ኮፒ (የአሜሪካ ዜጋ ላልሆኑ)

4)

መጠየቂያ ቅጽ መሙላት (Click here to download FORM)

5)

የሚያስገቡት እቃዎች ዝርዝር በሁለት ኮፒ (Click here to download FORM)

6)

ኢትዮጵያ የቆይታ ጊዜ ማረጋገጫ (Click here to download FORM)
7) አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
8) በኖተሪ የተረጋገጠ መኪና የተገዛበት ደረሰኝ /Commercial Invoice/