LAISSEZ PASSER

The Embassy of Ethiopia issues a laissez-passer for Ethiopian nationals who have an emergency need to travel to Ethiopia urgently.

Please note that this document can only be used once to go back to Ethiopia. This is a temporary document.

Requirements for LAISSEZ PASSER :

  • Two recent, ears visible, color and passport size photograph with white background and the name of the applicant at the back of the photograph,
  • One filled out an application form with address, phone number, and signature (Click here to download)
  • One copy of the expired passport of personal information page, you don’t need to submit fingerprint,
  • One copy of a document that shows your current status in the US, i.e. Green card, I-94, or work permit
  • Processing fee $120.00 in money order payable to Ethiopian Embassy,

Applications can be made in person at the Embassy or through the mail with a self-addressed return envelope which has a tracking number (FedEx, or USPS Priority and USPS EXPRESS MAIL) with it.

The Embassy mailing address is the following:

Ethiopian Embassy Address

Embassy of Ethiopia
3506 International Dr NW
Washington, DC 20008

የይለፍ (የጉዞ)ሰነድ(Laissez-Passer)

ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለውና ከዚህ በፊት ፓስፖርት የነበረውና የፓስፖርቱ ጊዜ በማለቁ  ምክንያት አስቸኳይ ጉዞ ሲያጋጥመው የይለፍ ሰነድ መጠየቅ ይችላል፡፡ ሆኖም የይለፍ ሰነዱ የሚያገለግለው ወደ ኢትዮጵያ ለሚደረግ ጉዞ ብቻ ሲሆን በዚሁ የጉዞ ሰነድ ከኢትዮጵያ ለመመለሻ አያገለግልም፡፡ ጊዘው ያለፈበት ፓስፖርት ኢትዮጵያ ከሄዱ በኋላ ፓስፖርታቸውን ማሳደስ ይኖርባቸዋል፡፡

የይለፍ ሰነድ (ሊሴ-ፓሴ) ሲፈልጉ የሚከተሉትን አሟልተው ማቅረብ ይጠበቃል፤

  • የፓስፖርት መጠን ብዛት ሁለት ፎቶግራፍ የቅርብ 6 ወር ያልሞላው፤ ሁለቱንም ጆሮ የሚታይ፤ ባለ ቀለም(color) እና ከጀርባው ስም የተጻፈበት
  • የፓስፖርት ማመልከቻ ቅጽ ስም፤ የትውልድ ቀን፤ ወር፤ ዓመተምህረት እና የትውልድ ቦታ በፓስፖርቱ መሰረት የተሞላ፤የወላጅ ስም፤ዜግነትና አድራሻ እንደዚሁም የአመልካቹ አድራሻና ፊርማ (Click here to download)
  • አንድ የፓስፖርት ኮፒ ፎቶግራፍ ያለበት ገጽ
  • የግሪን ካርድ ፤ የመኖርያ ፈቃድ ወይም I-94 አንድ ኮፒ
  • የአገልግሎትክፍያ $120.00 በመኒ ኦርደር( money order) ለኢትዮጵያ ኢምባሲ ተብሎ የተጻፈበት
  • ወደ አመልካቹ የሚመለስበት ደረጃውን የጠበቀ ፖስታ በቂ ቴምብር ያለውና ከእነ ትራኪንግ ቁጥር(stamp with tracking number፣ለምሳሌ USPS priority, FedEx and USPS Express Mail) አድራሻ የተጻፈበት ፖስታ ከዶክመንቱ ጋር ማቅረብ ግዴታ ነው፤ የተሳሳተ አድራሻ እና ደረጃውን ያልጠበቀ ፖስታ ጋር ለሚከሰተው ችግር ኢምባሲው ተጠያቂ አይደለም፡፡

የኢትዮጵያ ኢምባሲ የፖስታ መለኪያ አድራሻ

Embassy of Ethiopia

3506 International Dr. NW

Washington, DC 20008