አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተመንግስት ተገናኝተዋል።
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተመንግስት የመጀመሪያ ግንኙነታቸዉን አካሂደዋል። አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ነጩ ቤተመንግስት ሲደርሱ በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚያንጸባርቅ ዲፕሎማሲያዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ይኸው ግንኙነት በቀጣይ ጊዜአት ለሚደረጉ በርካታ ውይይቶች መጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ኢትዮጵያና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በሁለቱ አገራት መካከል እንደ ሰላም፣ ጸጥታና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ጠንካራ አጋርነት ከመፍጠር አንጻር ያሉ ዕድሎችም ሰፊ ናቸው። አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም በውይይቱ ወቅት የተገኙትን ስቴት ሴክሬተሪ ማርኮ ሩቢዮ ጋርም ተገናኝተዋል።





H.E. Binalf Andualem, Ambassador Extraordinary and Plenipotentiary of Ethiopia to the United States, held his first meeting with President Donald J. Trump at the White House. He received a formal diplomatic welcome, which reflects the longstanding relationship between Ethiopia and the United States. This meeting marks the beginning of many future discussions. The potential for a strong partnership in areas such as peace, security, and economic cooperation between the two countries is limitless. Ethiopia and the United States have enjoyed a robust relationship that spans over 120 years. During this occasion, the Ambassador also had the opportunity to meet with Secretary of State Marco Rubio.
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!