ክቡር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ከተከበሩ ኮንግረስማን Jerry L. Carl እና ኮንግረስማን Ronny Jackson ጋር ተገናኝተው
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ከተከበሩ ኮንግረስማን Jerry L. Carl እና ኮንግረስማን Ronny Jackson ጋር ተገናኝተው በኢትዮጵያ እና አሜሪካ ግንኙነት ዙሪያ ተወያዩ። በውይይታቸው ሁለቱ ሀገሮች ከ120 አመታት በላይ የቆየ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን እንዲሁም በአፍሪካ በህዝብ ብዛት ሁለተኛ የሆነችው ሀገራችን በፈጣን የኤኮኖሚ ዕድገት ላይ እንደምትገኝ እና የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ ማሳደግ አስፈላጊ ስለመሆኑ ተወያይተዋል።
በተጨማሪም በአፍሪካ ቀንድ ስላለው የሰላም እና መረጋጋት ሁኔታ፣ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ መፅደቅ፣ ስለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ የህዝብን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ በመንግስት እየተተገበረ ያለው መጠነ ሰፊ የሪፎርም ስራ፣ ስለ ባህር በር ጉዳይ፣ አጎዋ ለኢትዮ-አሜሪካ ንግድ ግንኙነት ያለውን ፋይዳና ኢትዮጵያን ከአጎዋ ዕድል ተጠቃሚነት ማግለል በድሃ ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር ኢትዮጵያ ኢንቨስት ባደረጉ የአሜሪካ ባለሀብቶች ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ስለመሆኑ ክቡር አምባሳደሩ ማብራሪያ እና ገለጻ ሰጥተዋል።