እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ! (January 6, 2021)
የዘንድሮውን የልደት በዓል የምናከብረው በዚህ ዓመት ያሳለፍነውን ፈታኝ ተጋድሎና ከፊታችን የሚጠብቀንን ወሳኝ ዕድል እያሰብን ነው። አሁን በፈተናና በዕድል መካከል እንገኛለን። ዓለምም የመጀመሪያውን የክርስቶስ ልደት ያከበረችው በፈተናና በዕድል መካከል ሆና ነበር። በአዳም በደል ምክንያት የመጣው የመከራ ዘመን እያለፈ፤ የመከራው ዋና ምንጭ የሆነው ዲያብሎስ፣ በማኅጸን በተጀመረ የማዳን ሥራ እየተሸነፈ፤ የጨለማው ንጉሥ እየተረታ፤ የዘመናት ቋጠሮ እየተፈታ ነበር። ከፊት […]
