በዲ.ኤም.ቪና አካባቢዉ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ማሰሪያ የመጨረሻ ዙር የነፃ ልገሳ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸዉ ተገለጸ፤
እ.ኤ.አ ጁን 19/2025 በዲ.ኤም.ቪ እና አካባቢዉ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት በተገኙበት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ማጠናቀቂያ ገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡ በዚህ ታላቅ ሀገራዊ ሁነት ላይ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሜሪላንድና በቨርጂኒያ (DMV) የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የግል ባላሃብቶች፣ አደረጃጀቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት አመራሮች፣ ታዋቂና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በተለይ ደግሞ ከዚህ ቀደም ለግድቡ ግንባታ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያከናውኑ የቆዩ […]