US Secretary of State Antony Blinken will Travel to Ethiopia tomorrow, March 14, 2023, leading a High Level US Delegation.
Mr. Blinken is expected to meet with H.E Prime Minister Abiy Ahmed (Dr.), Deputy Prime Minister and Foreign Minister H.E Demeke Mekonnen and other top government officials to discuss bilateral, regional and multilateral issues of common interest.
For several decades, Ethiopia and the U.S. have been closely working on multifaceted areas of trade, peace and security, health, education, agriculture, humanitarian assistance and other sectors.
The Secretary’s visit to Ethiopia will help to revitalize and strengthen the longstanding cooperation of the two countries to the highest level it deserves.
Secretary Blinken is also scheduled to meet Chairperson of the AU Commission, Moussa Faki Mahamat.
Ethiopia and United States of America have 120 years of official diplomatic relationship.
photo: file
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚ/ር አንቶኒ ብሊንከን የተመራ የልዑካን ቡድን በነገው እለት (መጋቢት 5 ቀን 2015 ዓ.ም) ወደ ኢትዮጵያ ያቀናል።
ሚኒስትሩ በቆይታቸውም ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ ምክትል ጠ/ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮነን እና ሌሎ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
በዚህም በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያጎለብቱ ሃሳቦች ላይ የሚመክሩ ይሆናል።
ላለፉት በርካታ አስርት ዓመታት ሁለቱ አገራት በንግድ፣ በጸጥታና ደህንነት፣ በግብርና ልማት፣ በጤናና ትምህርት ማስፋፋት በሰብዓዊ ድጋፍ ወዘተ ዙሪያ በትብብር ሲሰሩ ቀይተዋል።
ይህ በአሁኑ ወቅተ የሚደረገው ጉብኝትም የአገራቱን ዘመናትን የተሻገር ጠንካራ መስተጋብር ወደሚመጥነው ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ለማሸጋገር አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
ሴክሬታሪ ብሊንከን በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊ/መንበር ሙሳ ፋኪ ማሀማት ጋር ተገናኝተው እንደሚነጋገሩም ይጠበቃል፡፡
ኢትዮጵያና አሜሪካ የ120 ዓመታት የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ታሪክ አላቸው፡፡
ምስል፡ ፋይል
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!