ህዳር 5 ቀን 2015 ዓ.ም በዲሲ የሰላም እና አንድነት ግብረ-ኃይል ከኤምባሲው ጋር በመተባበር በአገራችን ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተከናውኗል።

በእለቱም ክቡር አምባሳደር ስለሺ በቀለ ባሰተላለፉት መልዕክት በአሜሪካ የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት በአገራችን ተከስቶ በነበረው ጦርነት ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት እና የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
“አሁን ወደ ራሳችን የምንመለስበት፣ ጉዳታችንን የምንጠግንበት፣ አንዳችን ላንዳችን እንቅፋት ሳንሆን አለኝታ፣ ፈጥኖ ደራሽ፣ አጽናኝ፣ እና አስታዋሽ የምንሆንበት ወቅት ነው” ሲሉም ገልጸዋል።

እንደ ዲሲ ግብረሃይል ሁሉ ሌሎች አደረጃጀቶች እና መላው የዳያስፖራ ወገናችን የተጎዱትን በማጽናናት፣ በማስታረቅ፣ ለተራቡት በመድረስ፣ እውነተኛ እርቅ እና ዘላቂ መተማመን እንዲጸና ከምንጊዜውም በላይ በርትቶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ዝግጅቱን ያስተባበሩት የዲሲ የሰላም እና አንድነት ግብረ-ኃይል አባላት እና ተሳታፊዎችም የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲሚቀጥሉ እና በዳያስፖራው ዘንድም የበለጠ አንድነት እና ቅርርብ ተፈጥሮ ለአገር ገንቢ ሚና እንዲጫዎት የጀመሩትን ስራ እንደሚያሰፉ ገልጸዋል።
በእለቱም ከ80 ሺህ ዶላር በላይ ለማሰባሰብ ተችሏል። ይህን እንዲሳካ ለለገሱና ላስተባበሩ ሁሉ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ምስጋና አቅርበዋል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *