ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ከአልጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተነጋገሩ

(ህዳር 13 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ): ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ከአልጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ራምታን ላማምራን ጋር ዛሬ ተነጋግረዋል።
ኒጀር ርዕሰ መዲና ኒያሚ ውስጥ ነገ በሚጀምረው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ልዩ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ኒያሚ የሚገኙት ምክትል ጠ/ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በወቅታዊ የአገራችን ሁኔታና በደቡብ አፍሪካ የተፈረመው የሰላም ስምምነት ዙሪያ ለአልጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ላምምራ ገለፃ አድርገዋል።
አልጄሪያ አገራችን ፈተና በገጠማት ወቅት ለወሰደችው በመርህ ላይ የተመሠረቱ አቋሞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


የአልጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሰላም ስምምነቱ አፍሪካ የራሷን ችግር የመፍታት አቅም እንዳላት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት እና ደህንነት እንዲከበር አገራቸው እንደምትፈልግ ሚኒስትር ላማምራ ገልፀዋል። የኢትዮ-አልጄሪያ ወዳጅነት እንዲጠናከር በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *