“ሠላም ፍትህና ዕድገት ለኢትዮጵያ” ከተሰኘ የዳያስፖራ ምሁራን ህብረት ጋር ውይይት ተካሄደ

“ሰላም፣ ፍትህ እና ዕድገት ለኢትዮጵያ” የተሰኘ የዳያስፖራ ምሁራን ህብረት አባላት የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ከክቡር አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በበይነ-መረብ መድረክ ውይይት አደረጉ።
በውይይቱ ወቅት የህብረቱ አባላት በትኩረት ካነሱዋቸው ጉዳዮች መካከል በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵየዊያን ለሀገራቸው በእውቀታቸው፣ በገንዘባቸውና አቅማቸው በሚፈቅደው ሁሉ ለአገራቸው ሰላምና እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባቸው፣ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ አንዲፈቱ የሁሉም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ርብርብ ወሳኝ መሆኑን፣ አደረጃጀታቸው በቀጣይ የዳያስፖራው ማህበረሰብ አባላትን በማስተባበር ከሀገሪቱ ልማት ጎን መቆም ዋነኛ ዓላማቸው መሆኑን ያሳወቁት ተሳታፊዎቹ፣ በአገራችን የተከሰቱ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጽኑ እምነታቸው መሆኑን ከመግለጽ ባሻገር ለተግባራዊነቱም እንደሚንቀሳቀሱ ገልጸዋል።

ክቡር አምባሳደሩ በበኩላቸው የህብረቱ አባላት ለሰላም ያላቸውን ተነሳሽነት አድንቀው መንግስት ሁልጊዜም ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሠራ መሆኑን በመግለጽ፣ ከህብረቱ አባላት በአስተያየትና ጥያቄ መልኩ በተነሱ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ዝርዝር ማብራሪያና ምላሽ ከሰጡ በኋላ ኤምባሲው ሁለንተናዊ የዳያስፖራ ተሳትፎን ለማረጋገጥ በቀጣይ ከማህበሩ አባላት ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት ገልጸውላቸዋል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *