በመላው አሜሪካ የሚገኙ በኢትዮጵያውያን የተመሰረቱ የተለያዩ አደረጃጀቶች በኢትዮጵያ ላይ እየተደረጉ ያሉ ያልተገቡ ጫናዎችን ለመመከት በቅንጅት እንደሚሰሩ አስታወቁ። (June 15, 2021)

ከሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች የተውጣጡ በዳያስፖራ ኢትዮጵያውይን የተቋቋሙ ማህበራት እና የኮሚዩኒቲ አደረጃጀቶች ተወካዮች በተገኙበት የበይነ መረብ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ወቅት ክቡር አምባሳደር ፍጹም ባስተላለፉት ልዕክት እነዚህ አደረጃጀቶች የኢትዮጵያ ድምጽ እንዲሰማ እያደረጉ ላለው አስተዋጽኦ አመስግነው እየተደረገ ካለው ጫና አኳያ በበተለጠ ቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የየማህበራቱ ተወካዮችም በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው ያልተገባ ጫና እና የሃሰት ፕሮፖጋንዳ እስኪወገድ ድረስ ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴውን እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል። በመላው አሜሪካ ለሚኖሩ ዳያስፖራ ወገኖችም በዚህ ታሪካዊ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም አለኝታነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *