በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ዲፕሎማቶች ስልጠናዊ ምክክር የበይነ-መረብ ስልጠና ተካሂደ፣ (May 14, 2021)
በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኢምባሲ አምባሳደሮች፣ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ጋር በመንግስት አገልግሎት ዘርፍ የ10 ዓመት ፍኖተ- ካርታ ሰነድ ላይ ስልጠናዊ ምክክር በበይነ-መረብ ተካሂዷል፡፡
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የዋሽንግተን ዲሲ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኢምባሲ ክቡር አምባሳደር ፍጹም አረጋ እንደገለጹት ስልጠናው በቀጣዩ አስር ዓመታት በህዝብ የሚመረጥ መንግስት የሚነድፋቸውን የልማት እቅዶች ማሳካት የሚችል የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ የተላበሰ፤ነፃ ገለልተኛና ብቃት ያለው የመንግስት አገልግሎት ስርዓት ለመገንባት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
አያይዘውም የመንግስት አገልግሎት ዘርፉን ለመለወጥ በርካታ የለውጥ ፕሮግራሞች ተግባራዊ ሲደረጉ መቆየታቸውንና በዚህም ለውጦች እን ገልጸው፣ አሁን በአገራችን የተጀመረውን መጠነ ሰፊና ትልልቅ የሪፎርም ፕሮግራሞች ተፈጻሚ እንዲሆኑ የተዘጋጀው ፍኖተ-ካርታ ተግባራዊ እንዲሆን በጋራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በስልጠናው ነጻ፣ ገለልተኛና ብቃት ያለው አገልጋይ/ተቋም የመገንባት ሂደት፣ የሰው ሀብት የማልማት ስልት ከክህሎት ክፍተት ልየታ ተነስቶና በብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ታግዞ አቅም መገንባት፣ የመንግሥት ሠራተኞችን በጠንካራ ሥነ-ምግባር የታነጹ የማድረግና ዕሴት መገንባት እንዲሁም በመንግሥትን የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሸያ ግብ በበይነ-መረብ ወደሚቀርብበት ደረጃ ለማድረስ በመጀመሪያዎቹ የትግበራ ዓመታት ምቹ መደላደል መፍጠር ላይ ያተኮረ ነበር።
ስልጠናው ውይይቱ የተዘጋጀው በዋናው መስሪያ ቤት በለውጥ ማኔጅመንትና መልካም አስተዳደር ጽ/ቤት ሲሆን መንግስት ዜጋው/ህዝቡ የሚጠበቀውን አገልግሎት በብቃት መስጠት እንዲችል የተዘጋጀውን የለውጥ ሰነድ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅና መ/ቤታችን የለውጥ ማሻሻያ ፕሮግራሞቹ ወሳኝ በመሆናቸው ለተግባራዊነቱ የጋራ ስራ እንደሚያስፈልግ ስምምነት ላይ በመድረስ ተጠናቋል፡፡
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!