”በአፍሪካ አህጉር የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ትስስር በመፍጠር የወጣቶችን ተጠቃሚነት ማጎልበት ይገባል ።”የቀድሞ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ
(ጥቅምት 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ): እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ወጣቶች ጉባኤ የቀደሞ መሪዎች በፓን አፍሪካኒዝም ዙሪያ ለወጣቶቹ ያላቸውን ልምድ አካፍለዋል ።
በመድረኩ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የአፍሪካ ህብረት 2063 ፍኖተ ካርታ ለወጣቶች ትኩረት ይሰጣል፥ ፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ እና አስተሳሰብ እንዲያድግ እና በአህጉሩ እንዲጠናከር በርካታ ስራዎች መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ውህደት እንዲኖር በዓለምአቀፍ ደረጃ ጥረቶች መደረግ እንዳለባቸው የገለፁት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ የእረጅም ጊዜ ግጭትን በማስወገድ የመሰረተ ልማት ትስስርን ማጠናከር በልማት መስኮች እድሎች መፍጠር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የወጣቶችን አቅም መጠቀም እና የአመራር ሚናቸውን ማጎልበት ይገባል ብለዋል ።
የጋና የቀድሞው ፕሬዝዳንት ክቡር ድራማኒ ማሀማ አፍሪካ በቅኝ ግዛት ዘመን ያሳለፈችው ፈታኝ ጊዜ በማለፍ አሁን ባሉ ተስፋ እና እድሎች መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል ።
የአፍሪካ ባህላዊ እሴቶችን በማዳበር የራሳችን ሞራል እና ማንነት መጠበቅ ይገባል ፤ዛሬ በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ ሀሳቦች አፍሪካዊ ማንነታችን እያሳጡን በመሆኑ፤ የዚህ ዘመን ወጣቶች ይንን በመከላከል እና በመጠበቅ ወጣቶች ኃላፊነታችሁን መወጣት ይገባችኋል ነው ያሉት።
አፍሪካውያን በሰላም ግንበታ ፣ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ እና የተፈጥሮ ሀብትን በበቂ መጠን መጠቀም የነገ ትውልድ መሪዎች አቅም መገንባት ያስፈልጋል ተብሏል ።
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!