አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ለዓለም ለማሳወቅ በዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላካሄዱት ሰልፍ ምስጋናቸውን አቀረቡ (March 11, 2021)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገር ቤት ያለውን ትክክለኛ እና ወቅታዊ ገፅታ አስመልክቶ ላካሄዱት ሰልፍ ምስጋናቸውን አቀረቡ፡፡

አቶ ደመቀ ለሰፊው ዓለም እውነታውን ያስተጋባችሁበት ታሪካዊ ሰልፍ በእጅጉ የሚደነቅ ነው ሲሉ ነው በፌስቡክ ገጻቸው የገለጹት፡፡

ሰልፈኞቹን ለፈፀማችሁት አኩሪ ተግባር ከልብ እናመሰግናለን፤ ደግሞም ኮርተንባችኋል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ በሌሎች ክፍለ ዓለማት በኢትዮጵያ ምድር ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታለምዕራቡ ዓለም ለማስገንዘብ በታላቅ የንቅናቄ ሰልፍ ዝግጅት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንንም አበረታተዋል፡፡

አቶ ደመቀ ሰልፈኞቹን ታላቅ ምስጋና እና አክብሮታችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በቀጣይ ሁሉም እናት ሃገሩን ኢትዮጵያን ከፊት አስቀድሞ የፀና አንድነትን በማጥበቅ ወቅቱ ለሚጠይቀው ታሪካዊ ትግል በጋራ ሁሉም እንዲረባረብ አሳስበዋል፡፡

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *