ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝደንት ክቡር ሼህ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ የመሩት ልኡካን ቡድንን በዛሬው እለት ሐምሌ 18 ቀን 2015 ዓም በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ውይይት አካሂደዋል።

ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ በእለቱ ባደረጉት ንግግር የልኡካን ቡድኑ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ማለትም ዲኤምቪ ፣ ሚኒሶታ ፣ ዋሺንግተን ሲያትል እና ቴክሳስ ሂውስተን ያደረገዉ የስራ ጉብኝት የመጣበትን አላማ ለማሳካት ከፍተኛ ፋይዳ ያለዉ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሚገኙ የኢትዮጵያ የሙስሊም ዳያስፖራ ተቋማት ፣ አደረጃጀቶች እና ማህበረሰብ በሀገራቸዉ ጉዳይ ላይ ከአሁን በፊት ያደርጉ የነበረዉን አስተዋጽኦ እና ተሳትፎ ይበልጥ ያጠናከረ፤ ከትዉልድ ሃገራቸዉ ጋር እንዲተሳሰሩ የሚረዳ እንዱሁም ዳያስፖራዉን ለልማት ያነቃቃ ተግባር መሆኑን ጠቅሰው ኤምባሲዉ የሚሰራውን ሁሉአቀፍ የዲፕሎማሲ ስራ በተለይ ደግሞ የዳያስፖራ ተሳትፎና አገልግሎት ስራዎችን ለልኡካን ቡድኑ አብራርተዋል።

በሚኒሶታ የሚገኘው Islamic University of Minnesota ለክቡር ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እና ለአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንት ለሼህ ሱልጣን አማን ኤባ ላበረከተላቸው የክብር ዶክትሬት እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ ተናግረዋል።
ክቡር ሼህሐጅ ኢብራሂም ቱፋ በበኩላቸው በኤምባሲው ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበልና ገለፃ አመስግነው በተለያዩ ግዛቶች ከኢትዮጵያ ከሙስሊም ማህበረሰብና የተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር ያደረጉት ቆይታ የተሳካ እንደነበርና ኤምባሲው ያደረገው ድጋፍ ውጤታማ እንደነበር ገልጸዋል።
በተጨማሪም ኤምባሲው የሚያደርገው ዘርፈ-ብዙ የዳያስፖራ አገልግሎት የሚበረታታ መሆኑን አክለው ጠቅሰዋል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *