የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመገኘት በአሜሪካ ዲ ኤም ቪ እና አካባቢዉ የሚገኙ በኢንቨስትመንት እና ቢዝነስ የስራ መስኮች ላይ ከተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን የዳያስፖራ አባላት ጋር ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ ም ውይይት አድርገዋል።

በእለቱም የዲያስፖራ አባላቱ አዲስ አበባ ከተማ በብራዚል ሪዮ ዲጄኔሮ የ2022 ሚላን ፓክት አዋርድ እና በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄደዉ የC40 የአለም ከተሞች ስላሸነፈችው ሽልማት የተሰማቸዉን ኩራትና ደስታ ገልፀዋል።

ከንቲባ አዳነች እስካሁን የተገኙ ድሎችም ሆነ ፈተናዎችን ለመሻገር በሚደረገዉ እንቅስቃሴ ዉስጥ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሚና ወደር የለሽ እንደሆነም አንስተዋል።
አሁንም አዲስ አበባን ከዲፕሎማቲክ ማእከልነቷ ባሻገር ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነችና እንደ ስሟ አበባ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት: በኢንቨስትመንት፤ በመኖርያ ቤት ግንባታ: በንግድ ፤ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፤ በእውቀት ሽግግር ፤ የከተማዋን የጤና ቱሪዝም ማእከልነት እቅድ በማሳካት ፤ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡

የዲያስፖራ አባላቱም በሀገራቸው እየተካሄደ ባለው አጠቃላይ እንቅስቃሴና እየመጣ ባለው ለውጥ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው የከንቲባዋን ጥሪ መቀበላቸውና በሃገር ጉዳይ በንቃት መሳተፍ እንደሚፈልጉ አሳውቀዋል። ሆኖም ወደ ሀገር ሲመጡ የሚያጋጥማቸውን የቢሮክራሲ ችግሮች መንግስት እንዲቀረፍላቸው ጠይቀዋል፡፡
ከንቲባ አዳነችም ይህንን ችግር ለመፍታት ዋነኛው መፍትሄ ስርዓት (system) መገንባት እና ማጠናከር እንዳለበት ገልፀው ይህንን ማድረግ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በዚህ ዙርያም ዲያስፖራው በተለይ በቴክኖሎጂ አገልግሎትን ለማዘመን የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፍ አሳስበዋል።

በዋሽንግተን የኢፌዴሪ ኤምባሲ ምክትል ሚሲየን መሪ አምባሳደር ዘላለም ብርሃን በበኩላቸው በዳያስፖራው በኩል የቀረቡ ጥያቄዎችና የኢንቨስትመነት ፍላጎቶች እንዲስተናገዱ እንደ ድልድይ በመሆን የጀመረውን ጥረት እንደሚያጠናክር አስተዋውቀዋል።

አዲስ አበባ ለስሟ የሚመጥን የከተማ መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉላት ዳያስፖራው በእውቀቱና በገንዘቡ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *