የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአሜሪካና ካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት አደረገ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአሜሪካና ካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት በሚኖራቸው ተሳትፎና በሚጠበቅባቸው ድጋፍ ላይ ውይይት አደረገ።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፈን አርአያ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት ባልተግባባንባቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተመካክሮ መግባባት ለሀገራችን አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፣ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን ለዚህ የበኩላቸውን ገንቢ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡
ስለ ሀገራዊ ምክክር መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳብ፤ ኮሚሽኑ ስለተቋቋመበት ዓላማና ስለሚመራበት የህግ ማዕቀፍ እንዲሁም ኮሚሽኑ ስለሚከተለው የአሰራር ሥርዓትና እስካሁን ስላከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት ገለፃና ማብራርያም በሌሎች የኮሚሽኑ አባላት ተሰጥቷል፡፡
በተጨማሪም በመድረኩ ላይ ኮሚሽኑ በአሜሪካና በካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በትብብር ስለሚሰራባቸው መንገዶች የተለያዩ ምክረ-ሀሳቦች ከተሳታፊዎች መቅረባቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!