የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ አሜሪካ መግባቱ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ?? በዛሬው ምሽት ከጉያና ብሔራዊ ቡድን ?? ጋር ያደረገውን የወዳጅነት ጨዋታ 2- 0 በማሸነፍ በድል ተጠናቋል።
በቨርጂኒያ ሴግራ ፊልድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የአማካይ ተጫዋቹ ሽመልስ በቀለ በ11ኛው እና በ76ኛው ደቂቃ ለዋልያዎቹ የማሸነፊያ ግቦቹን ማስቆጠር ችሏል።
በርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በስታዲየም በመገኘት ድጋፋቸውን በማሰማት ተከታትለዋል።
ብሔራዊ ቡድኑ በአሜሪካ ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን ሐምሌ 29/2015 ከአትላንታ ሮቨርስ ክለብ ጋር ያደርጋል።
ድል ለኢትዮጵያ!
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!