የኢትዮጵያ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ዕድልና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎቿ (June 26, 2021)

ከ110 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ያላትና ከ80 በላይ ቋንቋዎችን የሚነገርባት ህብረ ብሄሯ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኢኮኖሚና ፖለቲካ መስክ መሪ ሀይል እንደሆነች ይታመናል፡፡ ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መፈጠሪያ፣ የጥቁር አባይ ምንጭና የቡና መገኛ መሆኗም አይዘነጋም፡፡

ይህቺ ድንቅና የረጅም ታሪክ ባለቤት የሆነቸው ሀገር ነጻነቷን ከወራሪዎቸ ጠብቃ የኖረችና የአፍሪካውያን የነጻነት ተምሳሌት ምድር ነች ፡፡ ስለዚህም ነው ነጻነታቸውን ከቅኝ ገዚዎች የተቀዳጁ የአፍሪካ ሀገራት በ1955 ዓ.ም ግንቦት 16 ቀን በአዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ያቋቋሙት፡፡ አዲስ አበባ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ከተማ የተባለችውም በምክንያት ነው፡፡

ለ17 አመታት ኢትዮጵያን ያስተዳደረው ወታደራዊው ደርግ የሶሺያሊስት ርእዮተ አለም በመከተል ፋብሪካዎችን፣ ሰፋፊ እርሻዎችንና የከተማ ቤቶችን በመውረሱ የግሉ ዘርፍ እንዲቀጭጭና የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት እንዲገታ አድርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት በመጥፋቱ በርካታ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ በመሰደድ ኢኮኖሚው ላይ ጫና አሳድረዋል፡፡

ከደርግ ውድቀት ሶስት አስርት አመታት በኋላ ኢትዮጵያ በአለም ፈጣን እድገት ካስመዘገቡ ሀገሮች መካከል አንዷ ለመሆን በቅታለች፡፡ አዲስ አበባም እንደቀድሞው የተጎሳቆሉ መንደሮች የሞሉባት ሳይሆን ያሸበረቀች የአፍሪካ መዲና በመሆን ላይ ትገኛለች፡፡ የግሉ ዘርፍ እያደገም በመምጣቱ በኢትዮጵያ ትላልቅና መካከለኛ ከተሞች የኢንዱስትሪውና የአገልግሎት ዘርፉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል፡፡

ይህም ሆኖ ግን ኢትዮጵያ ከ2010 ዓ.ም በፊት ባሉት ጊዚያት ጽኑ የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መዛባት ገጥሟታል፡፡ በመንግስት ይከናወን የነበረው የተጋነነ የልማት ስራ ደካማ የፕሮጀክት አፈጻጸምና ዝቅተኛ የውጭ ንግድ ታክሎበት አጠቃላይ የኢኮኖሚ አፈጻጸሙን በችግር የተተበተበ እንዲሆን አድጎታል፡፡ ይህ የተዛባ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ያለመኖር ህዝባዊ አመጽ ቀስቅሶ በ2010 ዓ.ም የመንግስት ለውጥ ማስከተሉ ይታወሳል፡፡ አዲሱ የለውጥ መንግስትም በግሉ ዘርፍ የሚመራና ዘላቂ የኢኮኖሚ አድግት የሚያመጣ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በማድርግ በመትጋት ላይ ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያን ለኢንቨስትመንት ምቹ የሚያደርጓት በርካታ እውነታዎች አሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከፏፏቴዎች እስከ ፍልውሀዎች የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብት የታደለች፣ በውሀ ሀይልና በከርሰ ምድር እንፋሎት ሀይል ማመንጨት የምትችል ሲሆን ይህን እምቅ ሀይል ለማልማት ለሟል በቁርጠኝነት ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ የናይልን ወንዝ 85 በመቶ የውሀ ሀብት የምታበረክትና በምስራቅ አፍሪካ ለግብርና ስራ የሚውል ለም አፈር ያላት ሀገር ነች፡፡ በቀንድ ከብት ሀብቷም ከአፍሪካ አንደኛ መሆኗንም ልብ ይሏል፡፡

ኢትዮጵያ ከ18 አመት በታች ያለው የሀገሪቱን ህዝብ ግማሽ የሚሆነው ህዝቧ የተሸለ የትምህርት እድለ እያገኘ እንዲሄድ በማድረግና የስራ እድል እንዲፈጠርለት በትጋት በመስራት ለሀገሪቱ እድገትና ልማት ወሳኝ ሀይል እንደሚሆን እሙን ነው፡፡ ከቅርብ አመታት ወዲህ በርካታ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በመገንባታቸው የአምራች እንዱስትሪው ዘርፍ ማንሰራራት ችሏል፡፡ የቱሪዝም ዘርፉም እየተስፋፋ በመምጣቱ የአገልግሎት ዘርፉም እያደገ እያሳየ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገሮች በአለም አቀፉ የትምህረትና የሳይንስ ድርጅት (UNESCO) በርካታ ቅርሶችን ያስመዘገበች ሀገር ነች፡፡ ለኢትዮጵያ የወደፊት ብሩህ ተስፋ አመላካች ከሆኑት በጎ ጅምሮች ወስጥ በትምህረት፣ በንጹም መጠጥ ውሀ፣ በንጽና አጠባበቅና በመሰረታዊ ጤና አገልግሎት እንዲሁም በአጠቃላይ ማህበራዊ አገልግሎት ከለላ መስክ የምታስመዘግባቸው ስኬቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

መንግስት የኢኮኖሚ መወቅራዊ ችግሩ በከተማና በገጠር የስከተለውን ድህነት እንዲሁም የኮቪድ 19 በኢኮኖሚው ላይ ያስከተለውን መቀዛቀዝ ከግምት ያስገባ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ማሻሻያው በመንግስት ግዙፍ የመዋለ ንዋይ ፍሰት የሚመራውን የኢኮኖሚ ልማት በመግታት ላይ ያተኩራል፡፡ የኢኮኖሚ ማሻሻያው የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባትን በማስተካከል፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን በመቅረፍ፣ ምቹ የስራ ከባቢ በመፍጠር የመዋለ ንዋይን ፍሰት በማሳደግ፣ የንግድና ምርት ማነቆዎችን በማሰውገድ፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን የስራ አፈጻጸም በማሻሻል፣ የመንግስትን ብድር በመቀነስ እንዲሁም የኢኮኖሚ እድገቱ በግሉ ዘርፍ እንዲመራ በማስቻል ላይ አተኩሯል፡፡

ይህ የኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን መሳብ ከፍተኛ አስተዋዕኦ እያደረገ ይገኛል፡፡ የቴሌኮም አገልግሎት ለግሉ ዘርፍ ክፍት መደረጉም በመንግስት በሞኖፖል ተይዞ የነበረው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣና ቀልጣፋ አገልገሎት ለተገልጋዩ እንደሚያስገኝም ይታመናል፡፡ የመንግስት የኢኮኖሚ ማሻሻያው የግል ዘርፉን ለማጠናከር፣ ውድድርን ለማጎልበትና የግል መዋእለ ነዋይን ለማሳደግ መዋቅራዊ ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ላይም ትኩረት ተደርጎበት እየተሰራ ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያ በቀየሰችው የእድገት ጎዳና እንድትገሰግስ ስልታዊ በሆነ ዘዴ የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተግባረዊ ማድረግ ይጠበቅባታል፡፡ የግሉን ዘርፍ ሚና ማጎልበት እድገትን ያፋጥናል፣ የስራ እድል ይፈጥራል፣ በመጨረሻም የኢትዮጵያን እድገት ይበልጥ ዘላቂ ያደርገዋል፡፡

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *