የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ከሚሲዮኑ ሰራተኞች ጋር ተወያዩ፤
ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ዋሽንግተን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች ጋር በሚሲዮኑ በመገኘት ውይይት ያካሄዱ ሲሆን በሚሲዮኑ ትኩረት ተሰጥቶ ሊተገበሩ በሚገባቸው እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ካነሷቸው ነጥቦች መሃከል ዲፕሎማቱና መላው ሰራተኛ በፖለቲካ ዲፕሎማሲ፣ ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ፣ ሃብት ማፍራት፣ ወጪ ቅነሳ እንዲሁም ዲያስፖራ ጉዳዮችና ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ በቡድን መንፈስ በመንቀሳቀስ የሚቆጠርና ውጤት ማስመዝገብ ላይ ትኩረት በማድረግ መሰራት እንደሚገባው አንስተዋል።
በኢትዮጵያ መንግስት እየተከናወኑ ያሉ ትልልቅ የልማት እንቅስቃሴዎችን በተገኘው አጋጣሚ ለአሜሪካ መንግስትና ባላብቶች እንዲሁም ለዲያስፖራው ማህበረሰብ በማስተዋወቅ የአገራችንን ገጽታ መገንባትና ኢንቨስተሮች ወደ አገራችን ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ በማስቻል ረገድ ትልቅ ስራ የሚጠይቅ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል።
በመጨረሻም ከሚሲዮኑ ሰራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ሰፋ ያለ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።




Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!