የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች፣ የሚሲዮን መሪዎች እና የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ሥልጠና በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ውሏል


(ታኅሣሥስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ): ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ፣ ተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች፣ የሚሲዮን መሪዎች እና ምክትል የሚሲዮን መሪዎች እየተሰጠ ያለው ሥልጠና በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ውሏል።
በሱሉልታ የአፍሪካ አመራር ልህቀት ማዕከል እየተሰጠ በሚገኘው ሥልጠና በዓባይ ውኃ እና ቀይ ባሕር ጂኦ ፖለቲካ እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ዙሪያ ገለፃ ተደርጓል።


በዓባይ እና ቀይ ባሕር ጂኦ ፖለቲካ ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ውብእግዜር ፈረደ (ዶ/ር) የሀይድሮ ዲፕሎማሲ፤ ናይል፣ ቀይ ባህር፣ እና የውሃ ፖለቲካ አንድምታ፣ የውሃ ደህንነት፣ አዲሱ አጣብቂኝ በተመለከተ ሰፊ ገለፃ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታሁን ጋረደው(ዶ/ር) በበኩላቸው የአየር ንብረት ለውጥ እና በCOP 27 ዋና ጉዳዮች፣ በኢትዮጵያ በኩል ቅድሚያ የምንሰጣቸው ጉዳዮች በሰፊዉ ገልፀዋል።
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣና አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ስለሺ በቀለ(ዶ/ር) የህዳሴው ግድብ አሁናዊ ሁኔታን፣ በሁሉም አቅጣጫዎች የፕሮጀክቱ ሂደትን በሚመለከት ገለፃ አድርገዋል።
በማጠቃለያውም ወቅትም አምባሳደሩ ለተነሱ ጥያቄወች እና አስተያየቶች ተጨማሪ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *