የጥምቀት በዓል በዋሽንግተን ዲሲ በትናንትናው እለት በድምቀት ተከብሯል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል ለምዕመኑ ቡራኬ ሰጥተዋል።
ብጽእነታቸው ባስተላለፉት መልዕክትም በአገራችን እያታየ ያለው የሰላም አየር ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ልዩነትን በውይይት የመፍታት ጅምር ብቸኛ አማራጭ ሊሆን እንደሚገባ እና ለዚህ ስኬትም ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።


ጥምቀት ከእምንቱ ታላቅነት ባሻገር የአገራችን የአንድነት እና የህብረት ምሳሌ መሆኑንና በዚህ አብነት በአገራቸን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ እና ተቋማትን መልስ ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ ዳያስፖራው የጀመርውን በጎ ስራ እንዲያጠናክር ኤምባሲው በኩል ጥሪ ቀርቧል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *