ዳላስ ቴክሳስ አዲስ ታሪክ ተሰራ! (August 9, 2021)
በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 10:00 ሰዓት እስከ እኩለ ሌሊት በዘለቀው የኢትዮጵያውያን የዳላስ አብሮነት ምሽት ድንቅ የአጋርነት መልዕክቶችን በማስተላለፍ በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በአንድ መድረክ ከ$140,000 የአሜሪካን ዶላር በላይ በማሰባሰብ አዲስ ክብረ ወሰን ተመዝግቧል!
ይህ ድጋፍ እንዲገኝ ላስተባበሩ ለኮሚቴው ሰብሳቢና አመራሮች፣ ለኃይማኖት አባቶች፣ ለመድረክ መሪዎች እንዲሁም በጨረታ ጭምር በተደጋጋሚ ለለገሳችሁ ሁሉ የከበረ ምስጋናችን ይድረሳችሁ!
በቀጣይ የዳላሶችን ፈለግ በመከተል በሌሎችም ከተሞች የተጠናከረ የአጋርነትና የልገሳ ፕሮግራም እንደሚካሄድ እንተማመናለን! ኢትዮጵያ በልጆችዋ ትከበራለች!
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!