ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “የ21ኛው ክፍለ ዘመን ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የባለብዙ ወገን ልማት ባንኮችን ሞዴል ማሻሻል” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ውይይት ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ ሰኔ 15/2015(ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “የ21ኛው ክፍለ ዘመን ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የባለብዙ ወገን ልማት ባንኮችን ሞዴል ማሻሻል” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።

በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው አዲስ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስምምነት ጉባኤ ላይ አራት ነጥቦችን አንሥተው አጽንዖት ሰጥተዋል።

ነጥቦቹም:-

1) ከዚህ በፊት ቃል የተገቡ ስምምነቶችን መተግበር እንደሚያስፈልግ
2) የኮንሴሽናል ፋይናንስ አቅርቦትን ማሳደግ
3) ወደ አረንጓዴ ልማት ሽግግር ለማድረግ ለሚያስፈልገው የገንዘብ ድጋፍ ጠንካራ ዘዴ መፍጠር እና
4) የዕዳ ቀውስን ማቆም መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *