በሰሜን ካሮላይና የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ከ41 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ አደረጉ (May 25, 2021)

በሰሜን ካሮላይና የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ከ41 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ አደረጉ።  

ድጋፉን የሰሜን ካሮላይና የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ኃይል ተወካዮች በኤምባሲው ተገኝተው ዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ.ም አስረክበዋል።

ክቡር አምባሳደር ፍጹም አረጋ በርክክቡ ወቅት ለአስተባባሪዎቹ እና ድጋፍ ላደረጉ ለጋስ ወገኖች ሁሉ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና በአገራችን ላይ የተከፈተውን ያልተገባ ጫና ለማክሸፍ የተደራጀ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን በማቋቋም እንዲሰሩም ጠይቀዋል።

የታስክ ፎርሱ አስተባባሪዎቹም ለታላቁ የህዳሴ ግድብ እና ሌሎች አገራዊ ፕሮጀክቶች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።

በቅርቡም በግዛቱ የሚኖሩ የዳያስፖራ ወገኖች የሚሳተፉበት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ የቢዝነስ፣ እና የድጋፍ ማሰባሰቢያ መድረክ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ ተደርሷል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *