አቶ ደመቀ መኮንን የአለምአቀፉ የጥቁር ህዝቦት የታሪክ የትምህርት የባህል ማዕከል ምክርቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ


(የካቲት 16 ቀን 2016ዓ.ም.አዲስ አበባ):-የቀድሞ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የአለምአቀፉ የጥቁር ህዝቦት የታሪክ የትምህርት የባህል ማዕከል ምክርቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ዛሬ ተመርጠዋል።
ማዕከሉ ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባካሄደው የመጀመሪያ ጉባኤ ላይ ነው አቶ ደመቀን በኘሬዝዳንትነት የመረጠው።በዚሁ ጉባኤ ላይ አቶ ፀጋዬ ጨማ የማዕከሉ ዋና ፀሐፊ ሆነው ተመርጠዋል ።

የጥቁር ህዝቦች ንቅናቄ መስራችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የማርከስ ጋርቬ ልጅ ጁሊየስ ጋርቬን (ዶ/ር) የካውንስሉ የበላይ ጠባቂ ሆነዋል።
የአለምአቀፉ የጥቁር ህዝቦት የታሪክ የትምህርት የባህል ማዕከል የጥቁር ህዝቦችን ታሪክ፣ ባህልና ቅርሶችን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅና ጠብቆ ለማቆየት የተቋቋመ ነው።ተቋሙ ከወራት በፊት መቀመጫውንም በአዲስ አበባ ማድረጉ ይታወቃል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *