128ኛዉን የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል

የካቲት 22/2016 ዓ.ም 128ኛዉን የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ”አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል በዩናይትድ ስቴትስ ምዕራባዊ ክፍል በሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት በበየነ መረብ በድምቀት ተከብሯል።

የእለቱ የክብር እንግዳ በአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ለዝግጅቱ ተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልዕክት የአድዋ ድል በዓል ለኢትዮጵያዊያኖች ብቻ ሳይሆን ለመላዉ ጥቁር ህዝቦች ኩራት መሆኑን አስታዉሰዉ ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን በአጠቃላይ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሁለተኛ ትዉልድ በሀገራችን አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም፣ እድገት እና ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች ዉስጥ የራሱን አሻራ ማሳረፍ እንደሚገባዉ ጥሪ አቅርበዋል።

በዚህ በቨርቹዋል በተዘጋጀው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ላይ የእምነት አባቶች፣ የኪነ ጥበብ ሰዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ ዳያስፖራ አደረጃጀቶች አመራሮች እና አባላት እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በዓሉን ለመዘከር የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ስራዎች እና የግንዛቤ ማስጨበጫ አጭር ጽሁፍ ቀርቧል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *