ኤምባሲዎች አድማሱና አውዱ የሰፋ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ማድረግ እንድሚጠበቅባቸው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ

(ጥር 18 ቀን 2016 ዓ.ም.አዲስ አበባ):-የኢፌዲሪ ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ዓመታዊው የአምባሳደሮች ውይይት ዛሬ ሲጠናቀቅ የስራ መመሪያ በሰጡበት ወቅት ሚሲዮኖች የዲፕሎማሲ አድማስ ከፍ በማድረግ የኢትዮጵያን ተፈላጊነት ተደራሽ እና ተደማጭነት እንዲጨምር ለማድረግ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ።

በማጠቃለያው ክቡር አቶ ደመቀ ያልደርሰንባችው አለም ሀገራት አከባቢዎች ትኩረት ሰጥተን ፣ግንኝነት እንዲጠናከር እንሰራለን እንዲሁም የሁለትዮሽ ግንኙት እንዲጠናከር አዳዲሰ ወዳጆችን ለማብዛት ብሪክስን ጨምሮ ፣በኢጋድ፣አፍረካ ህብረትን ፣የተባበሩት መንግሰታትን እና ለሎች ባለ ብዙ ወግኖች አስተዋጽኦ ለማድረግ ብለዋል።
በአፍረካ ቀንድ ፣ጎሮበቶቻን ዲፕሎማሲ በተመለከተ የበለጠ ዝግጅነት የሚጠይቅ በመሆኑ ተጨባጭ ፣ ሁኔታዎችን በመከተታል በጋራ እንሰራለን ።የኢኮኖሚ ዲፕሎማሰያችን የውጭ ግንኙነት ስራችን ከፍተኛ የትኩረት አቅጣጫ ሆኖ እንደሚቀጠል ገልጿል።
ከአገሮች ጋር ያለን የሁለትዮሽ ግንኘነት እንዲጠናከር እና የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያችን እንዲሰፋ በማድረግ የአገራችን ብሄራዊ ጥቅም ማረጋገጥ ይገባል ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ብለዋል ።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *