ክቡር አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከበድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙስሊም ድርጅት ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም የበድር ኢትዮጵያ ተወካዮች በቅርቡ ከእስልምና እምነት ተቋማት እና ከመኖሪያ ቤቶች ጋር በተገናኘ በተለይ በአዲስ አበባ ዙሪያ ተከስተዋል ያሏቸውን ችግሮች አንስተዋል።በድር ኢትዮጵያ ህገ-ወጥነተን እንደማይደግፍ፤ ይሁንና የሚወሰዱ እርምጃዎች ህዝቡን አደጋ ላይ በማይጥል፣ በውይይት እና ወደ ቅሬታ በማያስገባ መልኩ እንዲሆን ጠይቀዋል። ድርጅቱ በቀጣይም አባላቱን በማስተባባር ለአገር ልማት፣ ሰላምና መልሶ ግንባታ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክርም ተናግረዋል። ክቡር አምባሳደር ስለሺ በበኩላቸው የተነሱትን ጥያቄዎች እንደሚገነዘቡ፣ በድር ኢትዮጵያ አገራችን ኢትዮጵያ በገጠሟት ፈተናዎች ሁሉ አባላቱን አስተባብሮ የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ድጋፍ በማድረግ ላሳየው አጋርነት አመስግነዋል። ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። በድርጅቱ ተወካዮች በኩል የተነሱ ጥያቄዎችን እና በጽሁፍ የቀረቡ መልዕክቶችን ለሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት እንደሚያደርሱም ቃል ገብተዋል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *