ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. 16ኛው የአገራችን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዲሪ. ኤምባሲ ተከበረ

16ኛው የአገራችን የሰንደቅ ዓላማ ቀን “የሰንደቅ አላማችን ከፍታ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና” በሚል መሪ ቃል የሚሲዮኑ መሪ ክቡር አምባሳደር ስለሺ በቀለ(ዶ/ር) እና ሁሉም የሚሲዮኑ ሰራተኞች በተገኙበት ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ተከብሯል።

ክቡር አምባሳደር ስለሺ በቀለ በእለቱ ባስተላለፉት መልእክት ሰንደቅ አላማችን የአትዮጵያ ህዝቦች እኩልነት፣ አንድነት፣ ማንነትና ሕብረ-ብሄራዊነት መገለጫ እንዲሁም የሉዓላዊነታችን መሰረት መሆኑን ገልጸው ታሪክ ሠርተው ሰንደቅ አላማችንን ላስረከቡንን አባቶቻችን ምስጋና አቅርበዋል። አሁንም የአገር አንድነትና የባንዲራን ክብር ለማጽናት መሰዋትነት እየከፈለ ላለው ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊትን እና ለሌሎች የፀጥታ አካላት ትልቅ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
በመቀጠልም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደትናንተናው ትውልድ ሰንደቅ ዓለማችንን በተለያዩ መድረክ ላይ ከፍ ለማድርግ በቁርጠኝነትና በትብብርና መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በመጨረሻም ክብረ-በዓሉ የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር በመዘመርና ሰንደቅ ዓላማችን በመስቀል ተጠናቋል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *