በ1947 ዓም ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ባለ ጥቁርና ነጭ ፊልም በዲጂታላይዝድ መልኩ በኤምባሲው ለእይታ በቃ

በ1947 ዓ.ም ተሰርቶ ለእይታ የበቃው እና በአገራችን የመጀመሪያው ባለ ጥቁርና ነጭ ፊልም የሆነው “ሂሩት አባቷ ማነው” የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው በተገኙበት በዋሺንግተን ዲሲ ኤምባሲ ለእይታ ቀርቧል።
ፊልሙ ከ57 ዓመት በኋላ በዲጂታላይዝድ መልኩ ተሰርቶ ለህዝብ ለዕይታ መብቃቱ መንግስት የኪነ-ጥበብ ስራዎችን ለማሰደግ የሰጠውን ትኩረት አንዱ ማሳያ ነው። ቀደምት የኪነ-ጥበብ ስራዎችን ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ዲጂታላይዝ ተደርጎ ለህዝቡ እንዲደርስ መደረጉ የአሁኑ ትውልድ ትላንትን ከዛሬ አገናኝቶ መመልከት እንዲችል የሚረዳ ከመሆኑም ባሻገር የአገራችንን ታሪክን ለማወቅ ትልቅ እድል ይፈጥራል።

የአሁኑ ትውልድ፣ በተለይም በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን እውቀታቸውንና መዋለንዋያቸውን በማፍሰስ የአገራችንን ኪነ-ጥበብ ስራዎችን ለማሳደግና የራሳቸውን አሻራ ለማስቀመጥ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ተደርጓል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *