በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት በሳን ሚጌል አካባቢ የሚገኘው የአንድነት ገዳም ከሚያዚያ 15 2015 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

በቅርቡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ከምዕመኑ እና ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በተደረገ ድጋፍ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት በሳን ሚጌል አካባቢ ቦታ በመግዛት የሆህተ ሰማይ ወመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሃነስ ወቅድስት አርሴማ የአንድነት ገዳም የቤተ ክርስትያኗ ብጹዓን አባቶች፣ ምዕመኑ በተገኘበት ከሚያዚያ 15 2015 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
ገዳሙ ከሚሰጠው መንፈሳዊ ተልኮ ባሻገር በአሜሪካ ብሎም በተለያዩ የአለም ክፍልች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን የአገራቸውን ባህል፣ እሴቶችና በጎ ምግባርን የሚማሩበት ሁለገብ የአንድነት ማዕከል እንደሚሆንም ነው በእለቱ የተገለጸው።
በአሜሪካ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ እንደገለጹት ዘመናዊ ትምህርት ባልተስፋፋበት፣ ስልጣኔ እንደሰማይ ሩቅ በነበረበት ዘመንም ቤተክርስታያን ቁርበት ፍቃ፣ ቀለም በጥብጣ፣ በኢትዮጵያ ምድር የእውቀት ብርሃን እንዲፈነጥቅ አድርጋለች።
የተመሰረተው ገዳምም ከሃይማኖታዊ ተልዕኮው የሚሻገር ሁሉን አቀፍ የማህበረሰብ ልማት ማበልጸጊያ፣ የመላው የኢትዮጵያ ልጆች መሰባሰቢያ የአብሮነት ማዕከል ጭምር እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ገዳሙ እቅዱ መሰረት የኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ፣ የህብረትና የእውቀት ማዕከል ይሆን ዘንድ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት የኤምበሲው ድጋፍ እንደማይለይም ገልጸዋል።
ይህ ገዳም እንዲመሰረት ሃሰብ ከማመንጨት ጀምሮ አጠቃላይ ሂደቱን በኃላፊነት የመሩት የሰሜን ካሊፎርኒያና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ በበኩላቸው ገዳሙ የአገራችን ታሪክ ወደ አዲሱ ትውልድ የሚሸጋገርበት የኢትዮጵውያን ሃብት ነው ብለወል።
የኢትዮጵያን ረጂም ዘመን የተሻገረ ጥበብ፣ ታሪክ፣ የእደ ጥበብ ሙያዎች፣ ቋንቋ እና ሌሎች የሙያና የስነ ምግባር ላይ የሚያተኩሩ እስከ ዩኒቨርስቲ የሚደርሱ የትምህርት ማዕከላት እንደሚገነቡም ብጹ” አቡነ ቴዎፍሎስ ተናግረዋል።
ለገዳሙ መመሰርት በገንዘብ በእውቀትና በጸሎት የተረዱትን ሁሉ ያመሰገኑት ብጹ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ አብዛኛው ስራ ወደፊት የሚከናወን በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፉን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
ለገዳሙ ምስርታ የቦታ መግዣ ገንዘብ በማሰባሰብ እና በአጠቃላይ በደጋሙ መስርታ ሂደት አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦች እና ተቋማትም የእውቅና ሰርትፊኬት ተበርክቶላቸዋል።
ካሊፎርኒያን ጨምሮ ከአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች፣ ከካናዳ፣ ከአውሮፓ፣ ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአለም ክፍሎች የመጡ በዝግጅቱ ታድመዋል።
ይሄን መሰል መንፈሳዊ አስተምህሮ ከስነ-ምግባር አስማምቶ ትውልድ ለማነጽ ለዚህ በመብቃቱ ደስታቸውን ገልጸዋል።
የገዳሙ ቋሚ ካቴድራል የሚሰራበት ቦታ ላይም ብጹዓን አባቶች እና ምዕመኑ በተገኘበት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።
0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *