ክቡር አምባሳደር በስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ረዳት ፀሃፊ ጋር ተወያዩ
ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም በስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ረዳት ፀሃፊ ቪንሴንት ዲ. ስፔራ ጋር በኢትዮጵያ ኤምባሲ ተገናኝተው በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እየተደረገ ያለውን ጥረት ጨምሮ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ የተለዋወጡ ሲሆን፣ ሁለቱ ሀገራት በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል። ምክትል ረዳት ፀሃፊው የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለኢኮኖሚያዊ ትብብር የሚሰጠውን ትኩረት አፅንዖት ሰጥተው የገለጹ ሲሆን፣ ክቡር አምባሳደሩ በበኩላቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ሪፎርምና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ አጋርነት ለማጠናከር ያላቸውን ጠቀሜታ አስረድተዋል።
H.E. Ambassador Binalf Andualem met with Vinny D. Spera, the Deputy Assistant Secretary of the Bureau of African Affairs of the State Department at the Ethiopian Embassy and discussed the ongoing efforts to achieve lasting peace in Ethiopia. They also exchanged opinions on regional and global issues and committed to coordinating their actions. The Deputy Assistant Secretary emphasized the current administration’s focus on economic cooperation, while the Ambassador provided an overview of the reforms taking place in Ethiopia and their importance for strengthening the economic partnership between the two countries.

Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!