ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአሜሪካ ምክር ቤት አባል ትሬንት ኬሊን በጽ/ቤታቸው ተቀበሉ
( ሰኔ 27 ቀን 2015ዓ.ም) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የአሜሪካ ምክር ቤት አባል ትሬንት ኬሊ ዛሬ (ሰኔ 27/2015 ዓ.ም) በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የተከበሩ ኬሊን ውይይት የኢትዮ አሜሪካ ወዳጅነት የበለጠ በሚጠናከርበት እና የአፍሪካ ቀንድ የሠላም እና ደህንነት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
የምክር ቤቱ ባለፈው ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኃላ ያደረጉት የመጀመሪያ ጉብኝት እንደሆነ ጠቅሰው ብዙ ጉዳዮች በበጎ ሁኔታ መለወጣቸውን መታዘብ እንደቻሉ ጠቅሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በአገሪቱ ሰላም እንዲመጣ እየወሰደ ያለውን በጎ ዕርምጃ አሜሪካ እንደምትገነዘብ ጠቅሰው ከሰብአዊ መብት ጋር በተያያዘ ተጥሎ የነበረው ገደብ መነሳቱ ግንኙነቱ ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡
ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ በመስጠት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የዳግም ግንባታና የመልሶ ማቋቋም ዕቅዶችን እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!