በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሐመድ እንድሪስ የሚመራው ልዑካን ቡድን ጉብኝት

በባልቲሞር ከተማ Keffa Coffee የተሰኘ በቡና ንግድ ዘርፍ ተሰማርቶ የሚገኘው ትውልደ ኢትዮጵያዊ አቶ ሳሙኤል ደምሴ ባለቤትነት የተቋቋመ የስፔሻሊቲ ቡና አስመጪ ድርጅት በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሐመድ እንድሪስ የሚመራው ልዑካን ቡድን ጉብኝት ተደረገ።

Keffa Coffee, Inc. በአሜሪካ በሚገኘው Walmart የመገበያያ ተቋም የተቆላ ቡና በማስረከብ እንደሚሸጡና እስካሁን ለ1500 የWalmart ሱቆች የአገራችንን የቡና ምርት ለአሜሪካ ገበያ እንደሚያቀርቡ የድርጅቱ ባለቤት አቶ ሳሙኤል ገልፀዋል።
በጉብኝቱ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተሰማርተው በሚገኙበት የንግድ መስክ ውጤታማ ሆነው እንዲቀጥሉና ሀገራቸውን በኢኮኖሚ መስክ በማገዝ የሚያበረክቱትን ድርሻ አጠናክሮ ለማስቀጠል ተቀራርቦ በመስራት ማበረታታት እንደሚገባ ዶ/ር መሀመድ እንድሪስ ገልፀዋል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *