በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያና የዳያስፖራ ሁለንተናዊ ተሳትፎን አስመልክቶ በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው የሚኖሩ ዳያስፖራዎችን ያሳተፈ የውይይት መድረክ በዋሺንግተን ዲሲ የኤፌዲሪ ኤምባሲ በሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓም ተካሄደ።

በውይይት መድረኩ ላይ ክቡር የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሰደር አርጋ፣ በዋሺንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር ክቡር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ እና በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶር መሀመድ እንድሪስ የሚመራው የልኡካን ቡድን አወያይነት በኤምባሲው ግቢ ተከናውኗል።
ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ በእለቱ ባደረጉት ንግግር በውጭ ሀገር የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ በጋራ በመሆን ሳይከፋፈሉ የሚገጥሙ ችግሮችን በአንድነት በመቆም መወጣት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶር መሀመድ እንድሪስ በእለቱ ነዋሪነታቸውን በዋሺንግተን ዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂንያ ግዛቶች ያደረጉ ዳያስፖራዎችን ባሳተፈው መድረክ ላይ በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ላይና ሁለንተናዊ የዳያስፖራ ተሳትፎን አስመልክቶ በተዘጋጀ የመነሻ ሰነድ ገለፃ አቅርበው ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማጠናከር በርካታ ስራዎችን እያካሄደ መሆኑን በገለፃቸው አንስተዋል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በኩል ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ክቡር አምባሳደር ስለሺ ዳያስፖራው እስካሁን ሲያደርግ የነበረውን ዘርፈ-ብዙ አስተዋፅኦ አገራቸው እንደምታመሰግናቸው ገልፀው ሚሲዮኑ በመንግስትና በዳያስፖራው መካከል ድልድይ በመሆን ያለውን ትስስር ለማጠናከር እንደሚሰራም አብራርተዋል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *