ታላቅ የውይይት ጥሪ ፤ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ (May 22, 2021)
በመላው አሜሪካ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ ወገኖቻችን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ:ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ “ለአገር ሉዓላዊነት በአንድነት” በሚል መሪ ቃል ክቡር አምባሳደር ፍጹም አረጋ በተገኙበት እኤአ ሜይ 22 ቀን 2021 ምሽት 6:00 PM ጀምሮ ታላቅ የዙም ውይይት አዘጋጅቷል። በውይይቱ በአሁኑ ወቅት እንደ አገር የገጠሙን ፈተናዎች እና መፍትሄዎቻቸው፣ የአገራት ጣልቃ ገብነት፣ የታላቁ ህድሴ ግድብ እና ሌሎች ታላላቅ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ ይደረጋል። የገጠሙን ፈተናዎች በድል ለመወጣት በአገር ውስጥም በውጭም የሚገኙ ኢትዮጵየታውያን ሚና ዙሪያም ምክክር ይደረጋል። ስለሆነም በዚህ ታላቅ ውይይት ላይ በመገኘት ለአገርዎ ያለዎትን አጋርነትን እንዲገልጹ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን። የዙም ውይይቱ መግቢያ አድራሻ ከታች ተያይዟል።
Meeting ID: 873 3525 1469
Passcode: 934218
https://us02web.zoom.us/j/87335251469?pwd=MHZwQS9YVmxOUVRQekFVZGU2WVhMdz09
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!