አምባሳደር ፍጹም አረጋ ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ለተውጣጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጡ። (July 1, 2021)
አምባሳደር ፍጹም አረጋ 592 ለሚሆኑ ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ለተውጣጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን መንግስት በትግራይ ክልል የወሰደውን የተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ እና ተያያዥ አገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
- መንግስት ከዚህ ውሳኔ የደረሰው የህግ ማስከበር ዘመቻው ግብ በመሳካቱ እንደሆነና አሸባሪው የህወኃት ቡድን ለአገር ደህንነት አደጋ በማይሆንበት ደረጃ ላይ በመድረሱ መሆኑን፣
- የትግራይ ገበሬም የክረምቱን ዝናብ ተጠቅሞ ሊያጋጥም ከሚችል ረሃብ ለመታደግ መሆኑን፣
- ፊታችንን ወደ ልማት መልሰን ሌሎች ስራዎቻችን ላይ ትኩረት ማድረግ ስለሚገባ፣
- ህይወት እያጠፉ እና እንቅፋት እየፈጠሩ በመንግስት ለማሳበብ የሚሰራን ሴራ ለማስቆም
የተወሰደ ፖለቲካዊ ውሳኔ መሆኑንና እስከ አዝመራው ወቅት የሚቀጥል መሆኑን አስረድተዋል።
የዳያስፖራ አባላት በኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ጫና ሲያሳድሩ የነበሩ ሚዲያዎችና የተለያዩ አካላት እውነቱን እንዲገነዘቡ የማድረጉን ስራቸውን እንዲያጠናክሩ አምባሳደር ፍጹም ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት እንዲወጣ ማድረጉ እና የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔው ለግዜው ግርታን ፈጥሮባቸው እንደነበር የውይይቱ ተሳታፊዎች የገለጹ ሲሆን፣ በተደረገላቸው ማብራሪያ የውሳኔውን ምክኒያታዊነት እንደተገነዘቡ ተናግረዋል።
በቀጣይም ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ሰላም እና ልማት የጀመሩትን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩ፤ በተለይም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገንዘብና የአድቮኬሲ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያላችውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!