ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የመጀመሪያውን ወርቅ በአትሌት ሰለሞን ባረጋ አገኘች (July 30, 2021)

ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የመጀመሪያውን ወርቅ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ውድድር በአትሌት ሰለሞን ባረጋ አግኝታለች።

አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያውን ያስገኘው በመጀመሪያው የኦሎምፒክ ተሳትፎው ነው።

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ዛሬ 8፡30 ላይ በተደረገው የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ ርቀቱን በ27፡43.22 በመግባት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ አስገኝቷል።

በውድድሩ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 4ኛ ሲወጣ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ደግሞ 8ኛ ሆኖ አጠናቋል።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *