ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን አስመልክቶ የበይነ መረብ ውይይት ተካሄደ።
በአሜሪካ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም በአሜሪካ በተለያዩ ስቴቶች ከሚኖሩ የዳያስፖራ አደረጃጀት፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና በውሃ ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማት አደረጃጀቶች አመራርና አባላት ጋር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የህዳሴ ግድብ በተለያየ ፈተና ውስጥ አልፎ ዛሬ እዚህ በመድረሱ እንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ይህ ፕሮጀክት የኢትየጵያን የመበልጸግ ፍላጎት እውን ከሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶች አንዱ በመሆኑ የቀረውን ሁለት በመቶ ለማጠናቀቅ እንደዚህ ቀደሙ አሻራችንን ለማስቀመጥ ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
አክለውም አገራችን እንድትበለጽግና ብሔራዊ ጥቅሟ እንዲረጋገጥ እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራት እንደሚያስፈልግ ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡




የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ግድቡ አሁን የደረሰበትን 98 በመቶ ለመድረስ ያለፈውን በጎ አጋጣሚና ተግዳሮቶች ላይ ሰፋ ያለ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ገለጻውን መነሻ በማድረግ ከዳያስፖራው ለተሰጡ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ዳያስፖራው ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡
ለግድቡ ማጠናቀቂያ የመጨረሻ ዙር ገንዘብ ማሰባሰብ ከተጀመረ ጀምሮ 28,338 የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም ቅዳሜ ሜይ 10/2025 በተካሄደው ገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ 4760 ዶላር በድምሩ 33,098 ገቢ የተደረገ ሲሆን 21,810 ዶላር በእለቱ ቃል ተገብቷል፡፡
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!