የማይቀርበት ታላቅ የበይነ መረብ (ዙም) ጉባኤ ጥሪ! የታላቁ አድዋ ድል 125ኛ ዓመት የድል በዓል መታሰቢያ (March 4, 2021)
በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ 125ኛው የአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ በመጪው ቅዳሜ ማርች 6/2021 ከቀኑ 12:00 PM (EST) ጀምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ አርቲስቶች፣ የኮሚኒቲ ተወካዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና መላው አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ለማክበር ዝግጅቱን አጠናቋል።
የእለቱ የክብር እንግዶች
ክቡር አቶ ደመቀ መኮነን – የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው – የኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
ክቡር አምባሳደር ፍጹም አረጋ – በአሜሪካ፣ ጃማይካ እና ፓናማ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር
በእለቱ የአድዋ ድል እና የአሁኑ ትውልድ አገራዊ ሃላፊነት ዙሪያ በምሁራን ገለፃ ይደረጋል፣ ተውኔት፣ ግጥምና እና የተለያዩ የጥበብ ስራዎች ይቀርባሉ።
ኑ ታላቁን ድል አብረን እንዘክር!
አድዋ የኢትዮጵያውያን አንድነትና የከፍታ ምልክት!
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!