የሰላምና አንድነት ማህበር የዋሺንግተን ዲሲ ግብረ ሃይል ተወካዮች በወቅታዊ የአገራችን ጉዳዮች ዙሪያ በኤምባሲያችን በመገኘት ውይይት አድርገዋል።
በግብረ ኃይሉ እና አጠቃላይ በዳያስፖራው ማህበረሰብ የሚነሱ ከሰላምና ጸጥታ፣ ከህገ-መንግስት እና ሌሎች ጉዳዮችን አስመልክቶ ጥያቄያቸውን በደብዳቤ ለክቡር አምባሳደር ስለሺ በቀለ ሰጥተዋል።
አምባሳደር ስለሺ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ባለፉት ዓመታት በአገራቸን ለውጥ እንዲመጣ ብሎም ሲደረጉብን የነበሩ ኢ-ፍትሃዊና ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ተጽእኖዎች በመቃዎም ግብረ ኃይሉ ላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግነዋል።
በቃል እና በደብዳቤ የቀረቡ ጥያቄዎችን ለሚመለከተው የመንግስት አካል እንዲደርስ እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል።
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!