የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት 12ኛ ዓመት የተመለከተ የዙም ውይይት በኤምባሲው አዘጋጅነት ተካሂዷል።
በእለቱም ይህ የአገር አንድነትና የልማት ቀንዲል ፕሮጀክት አጠቃላይ የግንባታ ሂደትና የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ በክቡር አምባሳደር ስለሺ በቀለ በኩል ገለጻ ተደርጓል።
ይህ ፕሮጀክት የመላው ኢትዮጵያውያን አሻራ ያረፈበት፣ የአገር አንድነት አቅም መገለጫ፣ በቅርቡም የሚሊዮኖችን ጓዳ በብርሃን ሊሞላ በግስጋሴ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።
ህዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአካባቢው ማህበረሰብ የበዛ ትሩፋት የሚያጎናጽፍ፤ የቀጣናው አብሮ የማደግ ማሳያ እንደሚሆን ነው የተጠቆመው።
ባለፉት ዓመታት በግንባታው ሂደት በፋይናንስ፣ በፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና በሙያ ሲያግዙ ለነበሩ በአገር ውስጥም በውጭም ለሚኖሩ ወገኖች ምስጋና ቀርቧል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሁሉን አቀፍ ድጋፋቸው እንደማይለይ ቃል ገብተዋል።
Dr Eng Seleshi Bekele
መጋቢት 24 ቀን 2015 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኤምባሲ,
ዋሽንግተን ዲሲ
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!