የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የመጀመርያውን ዙር የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ጥሪ ይፋ አደረገ! ሀምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ
ትረስት ፈንዱ በተቋቋመ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ካሰባሰበዉ ውስጥ ከ 116 ሚሊየን ብር በላይ አንገብጋቢ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በዘላቂነት ለሚፈቱ ፕሮጀክቶች ፈሰስ ያደርጋል
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ‘በቀን አንድ ብር ለወገን ክብር’ በሚል መርህ በ 77 ሀገራት የሚገኙ ከ24,000 በላይ ሀገር ወዳድ የዳያስፖራዉ ማህበረሰብ አባላት ካዋጡት ውስጥ 4,000,000 የአሜሪካ ዶላር (ከ 116,000,000 ብር በላይ) ለፕሮጀክቶች ትግበራ ለማዋል ቅደመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነዉ!
በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካኝነት ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ የተዋጣዉን ገንዘብ ሳይሸራርፍ እና ሳይጎድል በአስከፊ ድህነት ዉስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንን ችግር በዘላቂነት ለማቃለል ለሚችሉ የልማት ፕሮጀክቶች ትግበራ ለማዋል ቃል በገባነዉ መሰረት እነሆ ዛሬ ሓምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የመጀመርያውን ዙር የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ጥሪ ይፋ አድርጓዋል። ከተዋጣዉ ውስጥ 4,000,000 የአሜሪካ ዶላር ሙሉ በሙሉ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ ለማድረግ የሚዉል ሲሆን ማናቸዉም አስተዳደራዊ ወጪዎች ከዳያስፖራዉ መዋጮ ላይ አይሸፈኑም።
ህጋዊ እዉቅና ያላችው መንግስታዊ ያልሆኑ ሀገር በቀል የልማት ድርጅቶች፣ የህዝብ እና የሞያ ማህበራት ፣ የፌደራል እና የክልል የመንግስት ተቋሞች እንዲሁም ሰፊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸዉ ፕሮጀክቶችን የሚተገብሩ የግሉ ዘርፍ ድርጅቶች የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎቻቸዉን ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በመላክ የፋይናንስ ድጋፍ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ። የሚቀርቡት ፕሮጀክቶች የትረስት ፈንዱ ጽ/ቤት ባዘጋጀዉና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የዳይሬክተሮች ቦርድ ባጸደቀዉ የፕሮጀክቶች መመዘኛ እና መምረጫ መስፈርትና ስርዓት መሰረት ተገምግምዉ ይመረጣሉ። የምዘና እና መረጣ ስራዉ የሚካሄደዉ በፕሮጀክት ቀረጻ፣ ትግብራ እና ግምገማ ከፍተኛ ልምድ ባላችዉ በሀገር ዉስጥ እና በዳያስፖራ የሚገኙ ብቁ ባለሞያዎች ነው። ለአንድ ፕሮጀክት ትግበራ የሚመደበዉ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን 350,000 ዶላር (10,150,000 ብር) ሲሆን ዝቅተኛዉ ደግሞ 200,000 ዶላር (5,800,000 ብር) ነዉ።
የጤና፣ የትምህርት፣የዉሃ አቅርቦትና አገልግሎቶችን ማሻሻል፣ ለሴቶቸ እና ለወጣቶች የስራ ዕድል እና ገቢ የሚፈጥሩ አነስተኛ እና መሃከለኛ የንግድ ስራዎችን ማስፋፋት፣ የአካል ጉዳተኞችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል፣ የግብርና ምርታማነትን የሚያጎለብቱ አግልግሎቶችን ማሳለጥ፣ በእርስ በእርስ ግጭት ከመኖርያቸዉ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችሉ የመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት እንዲሁም ማህበራዊ አግልግሎቶችን የሚያፋጥኑ እና ስራ ፈጠራን የሚያበረታቱ ቴክኖሎጂዎችን መፍጥር እና ማስፋፋት በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ትኩረት ከሚሰጣቸዉ የልማት መስኮች ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ባወጣዉ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ እስከ መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ፕሮጀክቶችን የሚቀበል ሲሆን በቀጣይ ባሉት ሁለት ወራት ዉስጥ የፕሮጀክቶች ምዘና እና መረጣ ቡድኑ ስራዉን አጠናቅቆ የመረጣቸዉን ፕሮጀክቶች ለዳይሬክተሮች ቦርድ ለዉሳኔ ያቀርባል። በቦርዱ ይሁንታ ያገኙ ፕሮጀክቶች ከነዝርዝር መረጃቸዉ በህዳር ወር 2012 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረጉ ይጠበቃል። ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የፍይናንስ ድጋፍ የሚያኙ ፕሮጀክቶችን ትግበራ ለማረጋገጥም ጥብቅ የክትትል እና ግምግማ ስርዓት ይዘረጋል።
ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ጋር አብረዉ ለመስራት ፍላጎት ያላቸዉ እና የተሳተፎ መስፈርቱን የሚያሟሉ አካላት ስለፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች አቀራረብ፣ ምዘና እና አመራረጥ ስርዓት ዝርዝር መረጃ እንዲሁም አስፈላጊ የፕሮጀክት ማቅረብያ ቅጾችን እና ሰነዶችን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ድረ-ገጽ https://www.ethiopiatrustfund.org ማግኘት ይችላሉ፡፡ በስልክ ቁጥር +2519996864646 በመደወልም ተጨማሪ ማብራርያ መጠየቅ ይቻላል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ በቀን አንድ ዶላር በማዋጣት ለወገን ደራሽ እንዲሆን ጥሪ ካቀረቡበት ከ ሓምሌ 01 2010 ዓ.ም ጀምሮ ባለው አንድ አመት ውስጥ ከሃሳብ ወደ ተጨባጭ ትግበራ በመሸጋገር በርካታ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ለጥሪዉ መልስ ከሰጡ ከ24,000 በላይ ለጋሾች በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር መሰብሰቡ፣ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ዉስጥ ተቋቁሞ ህጋዊ እዉቅና በማግኘት ስራ መጀመሩ፣ በመላዉ አለም የሚገኙ ኢትዮጵዊያንን በማሰባብ የትረስት ፈንዱን አላማ ለመደገፍ በበጎ ፈቃደኝነት የሚሰሩ 39 የኢትዮጵያ የዜና እወጃ www.ethiopiatrustfund.org ለተጨማሪ መረጃ፡ ለሚዲያ ጥያቄ፡ ሀና አጥናፉ – የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የኮምንኬሽን ስፔሻሊስት +251 955 332 933 የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ጥሪን በተመለከተ፡ ፅጌረዳ ታፈሰ – የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የፕሮግራም ስፔሻሊስት +251 996864646 ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ቻፕተሮች መቋቋማቸዉ እንዲሁም ከሀገር ወዳድ የዳያስፖራ ለጋሾች የተሰበሰበዉን ገንዘብ ለፕሮጀክቶች ትግበራ ለማዋል የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ጥሪ መቅረቡ ተጠቃሽ ክንዉኖች ናችው። እነዚህን ውጤቶች እንድናስመዘግብ ያለመታከት ነፃ አግልግሎት በመስጠት ላይ ላሉት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የዳይሬክተሮች ቦርድ ፣ የአማካሪ ምክር ቤት አባላት እና በጎ ፈቃደኞች፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚገኘዉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ጽ/ቤት ለማቋቋም እና ስራዉን ለማሳለጥ ያልተቆጠበ ድጋፍ እና ትብብር እያደረገልን ላለዉ በኢትዮጵያ ለሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP Ethiopia) ምስጋናችንን አናቀርባለን። በተለይም ለሀገራዊ ጥሪያችን መልስ በመስጠት ለሀገራችሁ እና ለወገኖቻችሁ ያላችሁን ፍቅር በተግባር ላረጋገጣችሁ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ለጋሾቻችን ልባዊ ምስጋናችን እና ታላቅ አክብሮታችን ባላችሁበት ይድረሳችሁ።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በዳያስፖራ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ያለምንም የዘር፣ የብሔር፣ የቋንቋ እና የፖለቲካ አቋም ልዩነት ለኢትዮጵያዊያን ወገኖቻቸዉ ያበረከቱት ልዩ ስጦታ ነዉ። የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ከመንግስትም ሆነ ሌሎች አካላት ተጽእኖ ነፃ የሆነ ተቋም ነዉ።
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!