Entries by Embassy Content Editor

ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም አምባሳደር ቲቦር ናጊን በኤምባሲው ተቀብለው አነጋገሩ፤

በውይይታቸው የኢትዮጵያና አሜሪካን ግንኙነት ያለበትን ደረጃ የፈተሸ ጥልቅ ውይይት ያካሄዱ ሲሆን በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያግዙ መልካም ሀሳቦችን አንስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችው የሃገር-በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳዳር ለኢኮኖሚ ግንኙነት ከሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ጋር መገጣጠም ለሁለቱ አገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት የፈጠራቸው ልዩ እድሎችን አሟጦ መጠቀም በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል። በተጨማሪም የሁለቱ […]

Ethiopian Embassy Hosts Cultural Showcase in Washington, D.C.

The Embassy of Ethiopia in Washington, DC in collaboration with the International DC Club organized a promotional event aimed at showcasing Ethiopia’s tourism attractions. H.E. Binalf Andualem, Extraordinary and Plenipotentiary Ambassador of Ethiopia to the United States of America, delivered welcoming remarks, emphasizing Ethiopia’s deep-rooted cultural heritage. He highlighted the country’s UNESCO-recognized treasures, including the […]

ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት የአሜሪካ መንግስት ይደግፋል − በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ

ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የአሜሪካ መንግስት እንደሚደግፍ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ አስታወቁ፡፡ ኢትዮጵያ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት እያስመዘገበች መሆኗንም አምባሳደሩ አረጋግጠዋል። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሰላም እና ፀጥታ ለማረጋገጥ አሜሪካ ከወሳኝ አጋሯ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ እንደምትሰራም ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ የባህር በር ለማግኘት እንደምትሰራ በአጽንኦት መግለጻቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ […]

ክቡር አምባሳደር በስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ረዳት ፀሃፊ ጋር ተወያዩ

ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም በስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ረዳት ፀሃፊ ቪንሴንት ዲ. ስፔራ ጋር በኢትዮጵያ ኤምባሲ ተገናኝተው በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እየተደረገ ያለውን ጥረት ጨምሮ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ የተለዋወጡ ሲሆን፣ ሁለቱ ሀገራት በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል። ምክትል ረዳት ፀሃፊው የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለኢኮኖሚያዊ ትብብር የሚሰጠውን ትኩረት አፅንዖት […]

SelectUSA Investmenet Summit-2025 ላይ ለመሳተፍ ከኢትዮጵያ የመጡ ባለሀብቶች ጋር ውይይት ተካሄደ፤

በአሜሪካ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም SelectUSA Investmenet Summit-2025 ላይ ለመሳተፍ ከኢትዮጵያ የመጡ ባለሀብቶች ጋር በኤምበሲያችን ውይይት ያካሂዱ ሲሆን በመድረኩ የኢትዮ-አሜሪካ ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ ፕሬዝዳንትና ቦርድ አባላት፣ የአሜሪካ ኮሜርስ ዲፓርትመንት የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ዳይሬክተር እንዲሁም በአሜሪካ የዲ.ኤም.ቪና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች እና ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች፣ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላለፍዋል፡፡ […]

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ከሚሲዮኑ ሰራተኞች ጋር ተወያዩ፤

ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ዋሽንግተን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች ጋር በሚሲዮኑ በመገኘት ውይይት ያካሄዱ ሲሆን በሚሲዮኑ ትኩረት ተሰጥቶ ሊተገበሩ በሚገባቸው እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ካነሷቸው ነጥቦች መሃከል ዲፕሎማቱና መላው ሰራተኛ በፖለቲካ ዲፕሎማሲ፣ ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ፣ ሃብት ማፍራት፣ ወጪ ቅነሳ እንዲሁም ዲያስፖራ ጉዳዮችና ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ በቡድን መንፈስ […]

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኢቨንትስ ዲሲ ጋር ውይይት አደረገ

በአሜሪካ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም በዋሽንግተን ዲሲ የተለያዩ ታላላቅ ስብሰባዎችን፣ መዝናኛዎችን፣ ስፖርታዊ እና ባህላዊ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት የሚታወቀው ኢቨንትስ ዲሲ ፕሬዝዳንት እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስ ጌትስ እና ሎሎች አመራር አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል። ክቡር አምባሳደሩ ባደረጉት ንግግር የአዲስ አበባ እና የዋሽንግተን ዲሲ ከተሞች ያላቸው እህትማማች ግንኙነት ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከማጠናከር […]

ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን አስመልክቶ የበይነ መረብ ውይይት ተካሄደ።

በአሜሪካ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም በአሜሪካ በተለያዩ ስቴቶች ከሚኖሩ የዳያስፖራ አደረጃጀት፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና በውሃ ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማት አደረጃጀቶች አመራርና አባላት ጋር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የህዳሴ ግድብ በተለያየ ፈተና ውስጥ አልፎ ዛሬ እዚህ በመድረሱ እንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ይህ […]

ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ

ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የአሜሪካን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ላይ ገለጻ ለመስጠት እ.ኤ.አ. ሜይ 8 ቀን 2025 በጠሩት መድረክ ላይ ተሳትፎ አድርገዋል። በወቅቱም ክቡር አምባሳደሩ ከአሜሪካን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳኡ ጋር በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል። ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እየታየ ላለው አጠቃላይ ለውጥ እውቅና የሰጡ […]