ህዳር 5 ቀን 2015 ዓ.ም በዲሲ የሰላም እና አንድነት ግብረ-ኃይል ከኤምባሲው ጋር በመተባበር በአገራችን ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተከናውኗል።
በእለቱም ክቡር አምባሳደር ስለሺ በቀለ ባሰተላለፉት መልዕክት በአሜሪካ የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት በአገራችን ተከስቶ በነበረው ጦርነት ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት እና የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።“አሁን ወደ ራሳችን የምንመለስበት፣ ጉዳታችንን የምንጠግንበት፣ አንዳችን ላንዳችን እንቅፋት ሳንሆን አለኝታ፣ ፈጥኖ ደራሽ፣ አጽናኝ፣ እና አስታዋሽ የምንሆንበት ወቅት ነው” ሲሉም ገልጸዋል። እንደ ዲሲ […]
