የኢትዮጵያ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ዕድልና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎቿ (June 26, 2021)
ከ110 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ያላትና ከ80 በላይ ቋንቋዎችን የሚነገርባት ህብረ ብሄሯ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኢኮኖሚና ፖለቲካ መስክ መሪ ሀይል እንደሆነች ይታመናል፡፡ ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መፈጠሪያ፣ የጥቁር አባይ ምንጭና የቡና መገኛ መሆኗም አይዘነጋም፡፡ ይህቺ ድንቅና የረጅም ታሪክ ባለቤት የሆነቸው ሀገር ነጻነቷን ከወራሪዎቸ ጠብቃ የኖረችና የአፍሪካውያን የነጻነት ተምሳሌት ምድር ነች ፡፡ ስለዚህም ነው ነጻነታቸውን ከቅኝ ገዚዎች የተቀዳጁ የአፍሪካ […]
