SelectUSA Investmenet Summit-2025 ላይ ለመሳተፍ ከኢትዮጵያ የመጡ ባለሀብቶች ጋር ውይይት ተካሄደ፤
በአሜሪካ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም SelectUSA Investmenet Summit-2025 ላይ ለመሳተፍ ከኢትዮጵያ የመጡ ባለሀብቶች ጋር በኤምበሲያችን ውይይት ያካሂዱ ሲሆን በመድረኩ የኢትዮ-አሜሪካ ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ ፕሬዝዳንትና ቦርድ አባላት፣ የአሜሪካ ኮሜርስ ዲፓርትመንት የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ዳይሬክተር እንዲሁም በአሜሪካ የዲ.ኤም.ቪና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ባለሀብቶች እና ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች፣ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላለፍዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ለመጣው የባለሃብት ልዑክ እና እዚህ አሜሪካን አገር ለሚኖሩ ባላሃብቶች ይህንን አጋጣሚ በአግባቡ በመጠቀም እና ትርጉም ያለው ግንኙነት በመመስረት በሀገር ቤት ያለውን የኢንቨስትመንትና የገበያ እድሎችን ለመጠቀም በር የሚከፍት መሆኑን ክቡር አምባሳደሩ በመክፈቻ ንግግራቸው አንስተዋል፡፡
የኢትዮ-አሜሪካ ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ እና የአሜሪካ ኮሜርስ ዲፓርትመንት የአፍሪካ ጉዳዮች የአሜሪካ ባለሃብቶች ወደ ሀገራችን ገብተው ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት አማራጮችን መጠቀም እንዲችሉ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን ይህንኑ ለማገዝ ኤምባሲው እንደ ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን ገልፀዋል።
በኤምባሲው የተካሄደው ይህ ዝግጅት ከኢትዮጵያ የመጣው የባለሃብት ልኡካን ቡድን አሜሪካ ከሚገኙ አቻዎቻችው ጋር ግንኙነት በመመስረት ትስስር መፍጠር እንዲችሉና የነበረውን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መድረክ ነው፡፡





Meeting Held with Ethiopian Investors Attending SelectUSA Summit-2025
H.E. Binalf Andualem, Ambassador Extraordinary and Plenipotentiary of Ethiopia to the United States, hosted a discussion at the Embassy with Ethiopian investors participating in the SelectUSA Investment Summit 2025. During the forum, the Ambassador extended a warm welcome to the President and Board Members of the Ethio-American Chamber of Commerce, the Acting Director of African Affairs at the U.S. Department of Commerce, Ethiopian and Ethiopian-American investors residing in the DMV area, and other invited guests.
In his opening remarks, the Ambassador emphasized that the event creates an opportunity for the investor delegation from Ethiopia and those residing in the United States to build meaningful relationships and effectively capitalize on the investment and market opportunities available in Ethiopia.
The Ethio-American Chamber of Commerce and the African Affairs Office of the U.S. Department of Commerce encouraged American investors to explore the trade and investment opportunities available in Ethiopia and emphasized that the Embassy serves as a vital bridge to facilitate this engagement.
The event held at the Embassy served as a forum for the investor delegation from Ethiopia to connect with their American counterparts and to strengthen existing relationships.
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!